Skip to content

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ማለት ነው።

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ማለት ነው።

كان النبي صلى الله عليه وسلم يقول بين السجدتين: «اللَّهمَّ اغْفِرْ لي، وارْحَمْنِي، وعافِني، واهْدِني، وارزقْنِي».

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
በማመሳከሪያዎቹ ሐሰን ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላታቸው ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሙስሊም የሆነ ሰው በእጅጉ የሚፈልጋቸው ጉዳዮችንና የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም የሰበሰቡ የሆኑትን: ምህረትን፤ የወንጀል መሸሸግን፤ ይቅር መባልን መፈለግ፤ እዝነቱ እንዲያዳርሰው መፈለግ ፤ ከሚያምታታ፣ ዝንባሌው ከሚገፋፋውና ከበሽታዎችም ጤናማ መሆንን መፈለግ ፤ አላህን ለእውነትና በርሱ ላይ በመፅናት ላይ እንዲመራው መጠየቅ፤ የኢማን፣ የእውቀት ፣ የመልካም ስራ፣ ምርጥና ሐላል የገንዘብ ሲሳይ እንዲለግሰው መለመንን ሁሉ ያጠቃለሉ የሆኑትን እነዚህ አምስት ዱዓዎችን ይለምኑ ነበር።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በሁለቱ ሱጁዶች መካከል በምንቀመጥ ወቅት ይህ ዱዓእ መደንገጉን እንረዳለን።

ይህ ዱዓእ የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም ነገሮች ስለጠቀለለ የዚህ ዱዓን ትሩፋትንም እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (2/ 138) (850).

ሱነን ቲርሚዚ (1/ 317) (284).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (2/ 64) (898).

ሙስነድ አሕመድ (5/ 72) (2895).

ተጨማሪ (6)

مشكاة المصابيح.

للتبريزي (1/ 283).

سبل السلام شرح بلوغ المرام.

لمحمد الصنعاني (1/ 274).

توضيح الأحكام مِن بلوغ المرام.

لعبد الله البسام (2/ 240).