Skip to content

"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።"

ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:

"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።"

أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَقُولُ بَيْنَ السَّجْدَتَيْنِ: «رَبِّ اغْفِرْ لِي، رَبِّ اغْفِرْ لِي».

አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል በሚቀመጡ ጊዜ "ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ" "ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!" ይሉ ነበር። ይደጋግሟትም ነበር። "ረቢጝፊርሊ" ማለት አንድ ባሪያ ከጌታው ወንጀሎቹን እንዲምረውና ነውሮቹን እንዲሸሽግለት መፈለጉ ነው።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ይህንን ዱዓ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።

"ረቢጝፊርሊ" "ጌታዬ ሆይ! ማረኝ" የሚለውን ዚክር መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን። ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ማለት ነው።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (2/ 154) (874).

ሱነኑ ነሳኢይ (2/ 231) (1145).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (2/ 64) (897).

ሙስነድ አሕመድ (38/ 392) (23375).

ተጨማሪ (1)

نيل الأوطار (2/ 305).