"አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ።
ከአቡ ዘር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መካከል የተወሰኑት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሀብት ባለቤቶች በምንዳ ጥለውን ሄዱ። እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመው ይጾማሉ፤ በትርፍ ገንዘቦቻቸው ይመፀውታሉ።" እርሳቸውም "አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላበረደ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "እስኪ ንገሩኝ ብልቱን ሐራም ላይ ቢያኖራት ኖሮ ወንጀል አይኖርበትም ነበርን? ልክ እንደዚሁ የተፈቀደችለት ባለቤቱ ላይ ያኖራት ጊዜም ለርሱ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።»
أَنَّ نَاسًا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالُوا لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: يَا رَسُولَ اللهِ، ذَهَبَ أَهْلُ الدُّثُورِ بِالْأُجُورِ، يُصَلُّونَ كَمَا نُصَلِّي، وَيَصُومُونَ كَمَا نَصُومُ، وَيَتَصَدَّقُونَ بِفُضُولِ أَمْوَالِهِمْ، قَالَ: «أَوَلَيْسَ قَدْ جَعَلَ اللهُ لَكُمْ مَا تَصَّدَّقُونَ؟ إِنَّ بِكُلِّ تَسْبِيحَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَكْبِيرَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَحْمِيدَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَهْلِيلَةٍ صَدَقَةً، وَأَمْرٌ بِالْمَعْرُوفِ صَدَقَةٌ، وَنَهْيٌ عَنْ مُنْكَرٍ صَدَقَةٌ، وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةٌ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، أَيَأتِي أَحَدُنَا شَهْوَتَهُ وَيَكُونُ لَهُ فِيهَا أَجْرٌ؟ قَالَ: «أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهِ فِيهَا وِزْرٌ؟ فَكَذَلِكَ إِذَا وَضَعَهَا فِي الْحَلَالِ كَانَ لَهُ أَجْرٌ».
አንዳንድ ድሃ ሶሐቦች ያሉበትን ሁኔታና ድህነታቸውን፣ ብዙ ገንዘብ ያላቸው ወንድሞቻቸው ሶደቃ በመስጠት ብዙ ምንዳ እንዳገኙት እነርሱ ግን በድህነታቸው ምክንያት ይህን ብዙ ምንዳ ለማግኘት ሶደቃ መስጠት እንዳልቻሉና እንደነርሱ ብዙ መልካም ምንዳ የሚያገኙበትን መፍትሄ ፍለጋ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስሞታ አቀረቡ፡ ሀብታሞቹ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመውም ይጾማሉ፤ ሀብታሞች በትርፍ ገንዘቦቻቸው ምፅዋት ሲሰጡ እኛ ግን ምፅዋት አንሰጥም። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሊያደርጉት የሚችሉትን ሶደቃ በመጠቆም እንዲህ አሏቸው: "በራሳቹ ላይ የምትመፀውቱትን ነገር አላህ አላደረገላችሁምን? (ሱብሓነሏህ/ ጥራት ለአላህ የተገባው ነው) በማለታችሁ ለናንተ የሶደቃ ምንዳ ያስገኝላችኋል፤ ልክ እንደዚሁ (አሏሁ አክበር/ አላህ ታላቅ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (አልሐምዱሊላህ/ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (ላኢላሃ ኢለሏህ/ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከዚህም በላይ ሚስታችሁን መገናኘታችሁ ራሱ ሶደቃ ነው።" ሶሐቦችም ተገርመው "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላስደሰተ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "ንገሩኝ እስኪ ብልቱን ዝሙት ላይ ወይም ከዛ ውጪ በሆነ ክልክል ቦታ ላይ ቢያኖራት በርሱ ላይ ወንጀለኝነት አይኖርበትምን? ልክ እንደዚሁ የሚፈቀድለት ቦታ ላይ ካኖራት ደሞ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።
ሶሐቦች በመልካም ተግባር ላይ ያላቸው እሽቅድድምና ትልቅ ምንዳን ለማግኘትና አላህ ዘንድ ያለውን ትሩፋት ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ እንረዳለን።
የመልካም ተግባራት መንገዶች ብዙ እንደሆኑና አንድ ሙስሊም በመልካም ኒያና በጥሩ አላማ የሚሰራውን ስራ ሁሉ እንደሚያካትት እንረዳለን።
የእስልምና ገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን። ሁሉም ሙስሊም አላህን ለመገዛት አስቦ የሚሰራውን ስራ እንደየራሱ አለለት።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚፈቀዱ ነገሮች እውነተኛ ኒያ ተነይቶባቸው ከተሰሩ አምልኮ እንደሚሆኑ ማስረጃ ይሆናል። ግንኙነት ማድረግ የሚስትን ሐቅ ለመወጣት፤ አላህ ባዘዘው መልኩ በመልካም መኗኗር ተነይቶበት ወይም መልካም ልጅ ተፈልጎበት ወይም ነፍሱን ከዝሙት ለማቀብ ብሎ ወይም ሚስቱን ከዝሙት ለማቀብ ብሎና ወደ ሐራም ከመመልከት ወይም ስለርሱ ከማሰብ ወይም ስለርሱ ከማብሰልሰል ለመታቀብ ብሎ ወይም ከዚህ ውጪ ላሉ መልካም አላማዎች ነይቶበት ከሆነ የሚያደርገው አምልኮ ይሆንለታል።"
ሰሚው ነፍስ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባና ግልፅ እንዲሆን ምሳሌና ቂያስን ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
ሶሒሕ ሙስሊም (2/ 697) (1006).
ተጨማሪ (8)
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 201).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (2/ 161).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (3/ 31).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 150).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
10 መጻሕፍትተጨማሪ (10)
- الإسلام أصوله ومبادئه(وفي بضع أحدكم صدقة. قالوا: يا رسول الله! أيأتي أحدنا شهوته ويكون له فيها أجر؟ قال: أرأيتم لو وضعها في حرام أكان عليه وزر؟ فكذلك إذا وضعها في الحلال كان له أجر)[245].
- الخطب المنبريةموسوعة الخطب المنبرية (القسم الأول)«وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةٌ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ! أَيَأْتِي أَحَدُنَا شَهْوَتَهُ وَيَكُونُ لَهُ فِيهَا أَجْرٌ؟ قَالَ: «أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهَا فِيهَا وِزْرٌ؟ فَكَذَالِكَ إِذَا وَضَعَهَا فِي
- الصيام ومجموعة أسئلة في أحكامه«وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةً»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، أَيَأْتِي أَحَدُنَا شَهْوَتَهُ وَيَكُونُ لَهُ فِيهَا أَجْرٌ؟ قَالَ: «أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي الحَرَامِ، أَكَانَ عَلَيْهِ فِيهَا وِزْرٌ؟ وَكَذَلِكَ إِذَا وَضَعَهَا فِي ا
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا في حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهِ فيها وِزْرٌ؟ فكذلكَ إذا وضَعَهَا في الحَلاَلِ كانَ لَهُ أَجْرٌ».
- مجموعة زاد الحديث(2)1«أَوَلَيْسَ قَدْ جَعَلَ الله لَكُمْ مَا تَصَّدَّقُونَ؟ إِنَّ بِكُلِّ تَسْبِيحَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَكْبِيرَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَحْمِيدَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَهْلِيلَةٍ صَدَقَةً، وَأَمْرٌ بِالْمَعْرُوفِ صَدَقَةٌ، وَنَهْيٌ عَنْ مُنْكَرٍ صَ
- مجموعة زاد الحديث(2)1«أوَليس قد جعل الله لكم ما تَصَّدَّقُون؟!»
- مجموعة زاد الحديث(2)1«وفي بِضع أحدِكم صدقة»
- مجموعة زاد الحديث(2)1«أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهِ فِيهَا وِزْرٌ؟ فَكَذَلِكَ إِذَا وَضَعَهَا فِي الْحَلَالِ كَانَ لَهُ أَجْرٌ»،
- مجموعة زاد الحديث(2)1«وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةٌ».
- موسوعة الأسئلة (المجموعة الأولى)أَنَّ نَاسًا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ ﷺ قَالُوا لِلنَّبِيِّ ﷺ: يَا رَسُولَ اللهِ، ذَهَبَ أَهْلُ الدُّثُورِ بِالْأُجُورِ، يُصَلُّونَ كَمَا نُصَلِّي، وَيَصُومُونَ كَمَا نَصُومُ، وَيَتَصَدَّقُونَ بِفُضُولِ أَمْوَالِهِمْ. قَالَ: «أَوَلَيْسَ قَ