"ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። (ፍትሃዊ የሚባሉትም) እነዚያ በፍርዳቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በተሾሙበት ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያሰፍኑ ናቸው።"
«إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ اللهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ، عَنْ يَمِينِ الرَّحْمَنِ عَزَّ وَجَلَّ، وَكِلْتَا يَدَيْهِ يَمِينٌ، الَّذِينَ يَعْدِلُونَ فِي حُكْمِهِمْ وَأَهْلِيهِمْ وَمَا وَلُوا».
እነዚያ በአመራራቸውና በፍርዳቸው ስር ያሉ ሰዎችን እና በቤተሰቦቻቸው መካከል በፍትህና በእውነት የሚፈርዱ ሰዎች የትንሳኤ ቀን ለነሱ ክብር ይሆን ዘንድ ከፍ ባሉ ከብርሃን በተፈጠሩ ወንበሮች ላይ እንደሚቀመጡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። እነዚህም ወንበሮች በአርራሕማን ቀኝ በኩል የሚገኙ ናቸው። ጥራት የተገባው አላህ ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው።
المقسطين: العادلين.
في حكمهم: في قضائهم.
ما وَلُوا: الذي كانت لهم عليه ولاية.
የፍትህ ትሩፋቱና በሱ ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
ፍትህ በሰዎች መካከል ያሉ ሁሉንም ፍርድና ኃላፊነትን የሚያካትት ጠቅላይ ቃል ነው። በሚስቶች፣ በልጆችና በሌሎችም መካከል ፍትህ ማስፈን ሳይቀር ፍትሃዊነት ውስጥ ይገባል።
የትንሳኤ ቀን የፍትሃዊዎች ደረጃ መገለፁን እንረዳለን።
ሁሉም በስራው ልክ ስለሚመነዳ የትንሳኤ ቀን የኢማን ባለቤቶች ደረጃ የሚበላለጥ መሆኑን እንረዳለን።
በማነሳሳት የማስተማር ዘይቤ የሚማሩትን ሰዎች ትምህርቱን እንዲቀበሉ የሚያነሳሳ ከሆኑት የማስተማር ዘይቤዎች መካከል መሆኑን እንረዳለን።
ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1458) (1827).
ተጨማሪ (10)
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 547).
تطريز رياض الصالحين.
لفيصل المبارك (ص428).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (9/ 314).
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 710).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (3/ 640).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
3 መጻሕፍትተጨማሪ (3)
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 3«إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ الله عَلىٰ مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ: الَّذِينَ يَعْدِلُونَ في حُكْمِهِمْ وأَهْلِيهِمْ وَمَا وَلُوا».
- موسوعة الإيمان«إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ اللهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ عَنْ يَمِينِ الرَّحْمَنِ عز وجل، وَكِلْتَا يَدَيْهِ يَمِينٌ، الَّذِينَ يَعْدِلُونَ فِي حُكْمِهِمْ وَأَهْلِيهِمْ وَمَا وَلُوا».
- نبراس طالب (1)1«إِنَّ المُقْسِطِينَ عِنْدَ اللهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ... الَّذينَ يَعْدِلُونَ في حُكْمِهِمْ وَأَهْلِيهِمِ وَمَا وَلُوا»