'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
«لَا تَجْلِسُوا عَلَى الْقُبُورِ، وَلَا تُصَلُّوا إِلَيْهَا».
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መቃብሮች ላይ ከመቀመጥ ከለከሉ። ልክ እንደዚሁ ቀብሩ ወደ ሰጋጁ ቂብላ አቅጣጫ በሆነ ጊዜ ወደ መቃብሮች ዞሮ ከመስገድም ከለከሉ። ይህም የተከለከለው ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ አንዱ ስለሆነ ነው።
በሐዲሥ እንደተረጋገጠው የጀናዛ ሶላት ካልሆነ በቀር በመቃብር ስፍራ ወይም በመቃብሮች መካከል ወይም ወደ መቃብር ዙሮ መስገድ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ወደ መቃብር መስገድ የተከለከለው የሺርክን መዳረሻዎች ለመዝጋት ነው።
ኢስላም በመቃብር ወሰን ማለፍንም መቃብር ማዋረድንም ከልክሏል። በእስልምና ወሰን ማለፍም ማሳነስም የለምና።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "የሙትን አጥንት መስበር በህይወት እንደመስበር ነው።" ስላሉ የሙስሊም ክብር ከሞተ በኋላም ዘላቂ ነው።
ሶሒሕ ሙስሊም (2/ 668) (972).
ተጨማሪ (6)
توضيح الأحكام مِن بلوغ المرام.
لعبد الله البسام (2/ 30).
فتح ذي الجلال والإكرام شرح بلوغ المرام.
لمحمد العثيمين (1/ 522).
منحة العلام في شرح بلوغ المرام.
لعبد الله الفوزان (4/ 285).