"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
«إِنَّ اللهَ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ، وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ».
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ወደ ሰዎች ቅርፅና ሰውነት ያምራል ወይስ አስቀያሚ ነው? ትልቅ ነው ወይስ ትንሽ? ጤነኛ ነው ወይስ በሽተኛ? በማለት እንደማይመለከት ገለፁ። ወደ ገንዘቦቻቸውም ብዙ ነው ወይስ ትንሽ? በማለት አይመለከትም። አላህ ባሮቹን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባላቸው መበላለጥ ተንተርሶ አይቀጣቸውምም አይተሳሰባቸውምም። ነገር ግን በቀልቦቻቸው ውስጥ ወዳለው ፍራቻ፣ የእምነት እርግጠኝነት፣ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ፍፁማዊነት) ወይም የይዩልኝ ፣ የይስሙልኝ አስተሳሰብን ነው የሚመለከተው። ወደ ስራዎቻቸው ከመስተካከሏና ከመበላሸቷ አንፃር ይመለከትና በዛም መሰረት ይመነዳል።
ቀልብን ከሁሉም ውግዝ ባህሪያት ማስተካከልና ማፅዳት ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን እንረዳለን።
ቀልብ የሚስተካከለው በኢኽላስ ሲሆን ስራ የሚስተካከለው ደግሞ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመከተል ነው። አላህ ዘንድ ትኩረት የሚቸራቸውና ግምት ውስጥ የሚገቡት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።
የሰው ልጅ በገንዘቡም፣ በውበቱም፣ በሰውነቱም ሆነ በዚህች ዓለማዊ መገለጫዎች በአንዳችም ነገር መሸወድ እንደሌለበት እንረዳለን።
ውስጣዊ ማንነትን ሳያስተካክሉ ውጫዊ የሆኑ መገለጫዎች ላይ ከመደገፍ መጠንቀቅ እንዳለብን ተረድተናል።
ሶሒሕ ሙስሊም (2564) (4/ 1986).
ተጨማሪ (6)
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 40).
تطريز رياض الصالحين.
لفيصل المبارك (ص14).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 25).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
3 መጻሕፍትተጨማሪ (3)
- الخطب المنبرية موسوعة الخطب المنبرية (القسم الثاني)«إِنَّ اللَّهَ لَا يَنْظُرُ إِلَىٰ صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ، وَلَٰكِنْ يَنْظُرُ إِلَىٰ قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ»
- خطب تعظيم قدر الصلاة"إِنَّ اللهَ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ، وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ"
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (4)التربية الإسلامية 4«إِنَّ الله لا يَنْظُرُ إلى صُوَرِكُمْ وَأَمْوالِكُمْ، وَلَكِنْ يَنْظُرُ إلى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمالِكُمْ» وَأَشارَ بِأَصابِعِهِ إلى صَدْرِهِ.