"ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
"ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"
«حُجِبَتِ النَّارُ بِالشَّهَوَاتِ، وَحُجِبَتِ الْجَنَّةُ بِالْمَكَارِهِ».
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጀሀነም ክልክልን በመዳፈርና ግዴታን ባለመወጣት የመሰሉ ነፍስያ በምትፈልጋቸው ነገሮች መሸፈኗን መከበቧን ገለፁ። በመሆኑም የነፍስያውን ፍላጎት በዚህ ረገድ የተከተለ ለጀሀነም ተገባ። ጀነት ደግሞ ትእዛዝ ላይ በመዘውተር፣ ክልከላን በመተውና በዚሁ ላይ ትዕግስት በማድረግ በመሰሉ ነፍስያ በምትጠላቸው ነገሮች መሸፈኗንና መከበቧን አብራሩ። ስለዚህም በዚህ ረገድ በቁርጠኝነት ነፍስያውን የታገለ ለጀነት የተገባ ሆነ።
حُجبت: حُفت وأُحيطت.
በስሜት ላይ ለመውደቅ ሰበብ ከሚሆኑ መሰናክሎች መካከል አስቀያሚና የተወገዘ የሆነውን ነገር ነፍስያ ወዳው እስክትዘነበልለት ድረስ ሸይጧን ማስዋቡ አንዱ ነው።
ወደ ጀሀነም እሳት መዳረሻ ከመሆናቸው አንፃር ከተከለከሉ ፍላጎቶች መራቅና ወደ ጀነት የሚያደርሱ ከመሆናቸው አንፃርም የምንጠላቸው ነገሮች ላይ በመታገስ መታዘዛችንን እንረዳለን።
ነፍስያን መታገል፣ በዒባዳ ላይም መትጋት፣ በአምልኮ ዙርያ ያሉ የምንጠላቸውና የሚያስቸግሩን ነገሮች ላይም መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 102) (6487).
ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2174) (2822).
ሱነን አቡዳውድ (7/ 122) (4744).
ሱነን ቲርሚዚ (4/ 274) (2560).
ሱነኑ ነሳኢይ (7/ 3) (3763).
ተጨማሪ (10)
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (2/ 449).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (2/ 87).
المنهاج شرح صحيح مسلم بن الحجاج.
للنووي (17/ 165).
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 183).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمصطفى الخِن وغيره (1/ 134).