Skip to content

"አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

"አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»

«كل مُسْكِرٍ خَمْرٌ، وكل مُسْكِرٍ حرام، ومن شرِب الخمر في الدنيا فمات وهو يُدْمِنُهَا لَمْ يَتُبْ، لَمْ يَشْرَبْهَا في الآخرة».

ሙስሊም ዘግበውታል፤ አል ቡኻሪም የመጨረሻዋን ዐረፍተ ነገር ከእርሱ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውም አይምሮን የሚያደነዝዝና የሚያስወግድ የሚጠጣም ይሁን የሚበላም ይሁን የሚሸተት ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ነገር ሁሉ ኸምርና አስካሪ መሆኑን ገለፁ። ሁሉም አስካሪና አይምሮን የሚያስወግድ ነገርም አነሰም በዛም አላህ ከልክሎታል። ከነዚህ የአስካሪ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አይነት የወሰደና በመውሰድ ላይም የዘወተረ እስኪሞት ድረስም ንስሀ ያልገባ ሰውም ጀነት ውስጥ መጠጣትን በመነፈግ የአላህ ቅጣት ይገባዋል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የኸምር ክልክልነት ምክንያቱ ማስከሩ ነው። ስለዚህ ማንኛውም አይነት አስካሪ ክልክል ነው።

አላህ አስካሪ መጠጥን የከለከለው ትላልቅ ጉዳትና ብልሽቶችን ስለያዘ ነው።

ኸምርን ጀነት ውስጥ ሲሆን መጠጣቱ የድሎትና የእርካታ ማሟያ ነው።

በዚህ አለም አስካሪ መጠጥ ከመጠጣት ነፍሱን ያላቀበ አላህ ጀነት ውስጥ ከመጠጣት ይከለክለዋል። ምንዳ የሚሆነው በሰራው ስራ አይነት ነውና።

ከሞት በፊት ከወንጀሎች ንስሀ በማድረግ ላይ መቻኮል እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (7/ 104) (5575).

ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1587) (2003).

ተጨማሪ (15)

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (8/ 519).

فتح ذي الجلال والاكرام بشرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (5/ 418).

توضِيحُ الأحكَامِ مِن بُلوُغ المَرَام.

للبسام (6/ 307).

معالم السنن.

وهو شرح سنن أبي داود.

للخطابي (4/ 264).

الفتح الرباني لترتيب مسند الإمام أحمد بن حنبل الشيباني.

للساعاتي (16/ 116).

فيض القدير شرح الجامع الصغير.

للمناوي (5/ 30).

مرقاة المفاتيح شرح مشكاة المصابيح.

لعلي القاري (6/ 2382).