"እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»
ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው:
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»
«يَا أَيُّهَا النَّاسُ، أَفْشُوا السَّلَامَ، وَأَطْعِمُوا الطَّعَامَ، وَصِلُوا الْأَرْحَامَ، وَصَلُّوا بِاللَّيْلِ وَالنَّاسُ نِيَامٌ، تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ بِسَلَامٍ».
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መዲና መጥተው ሰዎች የተመለከቷቸው ጊዜ ወደርሳቸው አቅጣጫ በፍጥነት ሄዱ። ዐብደላህ ቢን ሰላምም ያኔ አይሁድ ነበርና ወደርሳቸው ከመጡት መካከል አንዱ ነው። እርሳቸውን ሲያይም በርሳቸው ላይ ብርሃንን፣ ውበትንና እውነተኛ ግርማን በማየቱ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቀ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት ለመጀመሪያ የሰማውም ነገር ሰዎችን ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆናቸውን ተግባራት ላይ ማነሳሳታቸውን ነው። መጀመሪያ: ባወቅከውም ይሁን ባላወቅከውም ሰው ላይ ሰላምታን ማሰራጨትና ማብዛት ነው። ሁለተኛ: ምግብን በሶደቃ፣ በስጦታና በእንግድነት መልክ ማብላት ነው። ሶስተኛ: በአባት ወይም በእናት በኩል ቅርበትና ዝምድና ከምትተሳሰርው አካል ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው። አራተኛ: ሰዎች በተኙበት ለሱና (ግዴታ ላልሆነ) ሶላት ሌሊት መቆም ነው።
በሙስሊሞች መካከል ሰላምታን ማሰራጨት እንደሚወደድ እንረዳለን። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ግን (አሰላሙ ዓለይኩም) በሚል ሰላምታ አይጀመሩም። ሙስሊም ያልሆነ ሰው ራሱ "አሰላሙ ዐለይኩም" በማለት ሰላምታን ካቀረበ "ወዐለይኩም" በማለት ይመለስለታል።
ሱነን ኢብኑ ማጀህ (4/ 397) (3251).
ሱነን ቲርሚዚ (4/ 264) (2485).
ሙስነድ አሕመድ (39/ 201) (23784).
ተጨማሪ (8)
توضيح الأحكام من بلوغ المرام.
لعبد الله البسام (2/ 454).
منحة العلام في شرح بلوغ المرام.
لعبد الله الفوزان (3/ 299).
فتح ذي الجلال والإكرام.
لابن عثيمين (6/ 440).
سبل السلام بشرح بلوغ المرام.
لمحمد الصنعاني (2/ 693).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
2 መጻሕፍትተጨማሪ (2)
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 6«أيُّهَا النَّاسُ: أفْشُوا السَّلامَ، وأطعمُوا الطَّعامَ، وصَلُّوا باللَّيل والنَّاسُ نيامٌ، تَدْخُلُوا الجَنَّةَ بسَلامٍ».
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «يَا أَيُّهَا النَّاسُ، أَفْشُوا السَّلَامَ، وَأَطْعِمُوا الطَّعَامَ، وَصَلُّوا وَالنَّاسُ نِيَامٌ، تَدْخُلُونَ الجَنَّةَ بِسَلَامٍ»