Skip to content
የሱራዎች ዝርዝር /

الحج

الحج is chapter 22 of the Quran and has 78 verses. This page presents it in full in the Uthmani script, with a verse-by-verse translation of its meaning.

78 አንቀጾች የሱራ ቁጥር 22
ወደ አንቀጽ ይሂዱ
አማርኛ · Zain
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمۡۚ إِنَّ زَلۡزَلَةَ ٱلسَّاعَةِ شَيۡءٌ عَظِيمٞ

እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና::

يَوۡمَ تَرَوۡنَهَا تَذۡهَلُ كُلُّ مُرۡضِعَةٍ عَمَّآ أَرۡضَعَتۡ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمۡلٍ حَمۡلَهَا وَتَرَى ٱلنَّاسَ سُكَٰرَىٰ وَمَا هُم بِسُكَٰرَىٰ وَلَٰكِنَّ عَذَابَ ٱللَّهِ شَدِيدٞ

በምታዩዋት ቀን ሁኔታው አጥቢ ሁሉ ያጠባችውን ልጅ ትዘነጋዋለች። እርጉዝ ሴት ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች:: ሰዎቹንም በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ መስለው ታያቸዋለህ:: እነርሱ ከመጠጥ የሰከሩ ሁው ሳይሆን ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ስለሆነ ነው።

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِي ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيۡطَٰنٖ مَّرِيدٖ

ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም የሚከተል ሰው አለ::

كُتِبَ عَلَيۡهِ أَنَّهُۥ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُۥ يُضِلُّهُۥ وَيَهۡدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ

እነሆ የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል:: ወደ አቃጣይ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል:: (ተወስኖባቸዋል)

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمۡ فِي رَيۡبٖ مِّنَ ٱلۡبَعۡثِ فَإِنَّا خَلَقۡنَٰكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ مِنۡ عَلَقَةٖ ثُمَّ مِن مُّضۡغَةٖ مُّخَلَّقَةٖ وَغَيۡرِ مُخَلَّقَةٖ لِّنُبَيِّنَ لَكُمۡۚ وَنُقِرُّ فِي ٱلۡأَرۡحَامِ مَا نَشَآءُ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى ثُمَّ نُخۡرِجُكُمۡ طِفۡلٗا ثُمَّ لِتَبۡلُغُوٓاْ أَشُدَّكُمۡۖ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرۡذَلِ ٱلۡعُمُرِ لِكَيۡلَا يَعۡلَمَ مِنۢ بَعۡدِ عِلۡمٖ شَيۡـٔٗاۚ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ هَامِدَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡ وَأَنۢبَتَتۡ مِن كُلِّ زَوۡجِۭ بَهِيجٖ

ሰዎች ሆይ! ከሞት በኋላ ከመቀስቀስ በመጠራጠር ጉዳይ እንደ ሆናችሁ የመጀመሪያውን (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ። እኛም) ከአፈር ፈጠርናችሁ:: ከዚያ ከፍትወት ጠብታ፤ ከዚያም ከረጋ ደም፤ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ። የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማህጸን ውስጥ እናረጋዋለን። ከዚያም ህፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን:: ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን):: ከናንተም መካከል በወጣትነቱ የሚሞት ሰው አለ:: ከናንተም መካከል ከዕውቀት በኋላ ምንንም ላያውቅ ወደ ጃጀ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ:: ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች \ትነቃነቃለች\:: ትነፋለችም:: ውበት ካለው የእጽዋት አይነት ሁሉ ታበቅላለችም።