Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 91 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (49)
መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ለሳቸውም እንዲህ አላቸው "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አቤት ብያለሁ" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አላቸው፦ "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" እሳቸውም፦ "የፈለግከውን ጠይቅ!" አሉት። እሱም፦ "በአንተና ከአንተ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቅሀለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች ባጠቃላይ የላከህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። እሱም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም በመቀጠል "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም "አዎን" አሉት። ሰውዬውም፦ "ይዘውት በመጡት አምኛለሁ፤ ከኋላዬ ካሉ ህዝቦቼ የተላኩኝ መልክተኛ ነኝ። እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): 'አሏሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወሚን ዓዛቢ‐ን‐ናር ወሚን ፊትነቲል መሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ‐ድ‐ደጃል' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።" 'ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' ማለት ነው። በሙስሊም ዘገባ ደግሞ 'አንዳችሁ ከመጨረሻው ተሸሁድ ያጠናቀቀ ጊዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ: ከጀሀነም ቅጣት፣ ከቀብር ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተናና ከመሲሕ ደጃል ክፋት።'ብለዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።