‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"»
ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«የአላህ መልክተኛ ነፃ ያወጡት ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ምክንያት ጀነት እንድገባ የሚያደርገኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»
لَقِيتُ ثَوْبَانَ مَوْلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقُلْتُ: أَخْبِرْنِي بِعَمَلٍ أَعْمَلُهُ يُدْخِلُنِي اللهُ بِهِ الْجَنَّةَ؟ أَوْ قَالَ قُلْتُ: بِأَحَبِّ الْأَعْمَالِ إِلَى اللهِ، فَسَكَتَ. ثُمَّ سَأَلْتُهُ فَسَكَتَ. ثُمَّ سَأَلْتُهُ الثَّالِثَةَ فَقَالَ: سَأَلْتُ عَنْ ذَلِكَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: «عَلَيْكَ بِكَثْرَةِ السُّجُودِ لِلَّهِ، فَإِنَّكَ لَا تَسْجُدُ لِلَّهِ سَجْدَةً، إِلَّا رَفَعَكَ اللهُ بِهَا دَرَجَةً، وَحَطَّ عَنْكَ بِهَا خَطِيئَةً» قَالَ مَعْدَانُ: ثُمَّ لَقِيتُ أَبَا الدَّرْدَاءِ فَسَأَلْتُهُ فَقَالَ لِي: مِثْلَ مَا قَالَ لِي: ثَوْبَانُ.
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት ለመግባት ሰበብ ስለሆነ ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስለሆነ ስራ ተጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂው እንዲህ አሉት: ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማብዛትን አዘውትር! አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም ቢምርህ እንጂ አንድም ሱጁድ ለአላህ አትወርድም።
ሶላት ሱጁድን ስለሚያካትት ግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ለመስገድ ጥረት በማድረግ ላይ ሙስሊሞች መበረታታታቸውን እንረዳለን።
የሶሐቦች ግንዛቤና እውቀት መገለፁ። ይህም ጀነት ከአላህ እዝነት በኋላ በስራ ካልሆነ በቀር እንደማትገኝ ማወቃቸው ነው።
ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማድረግ ደረጃን ከፍ ለማድረግና ወንጀሎችን ለማስማር ትልቁ ምክንያት ነው።
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 353) (488).
(4/ 205).
ተጨማሪ (9)
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين.
بهجة الناظرين.
لسليم الهلالي (1/ 188).
نزهة المتقين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 137).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (2/ 105).
شرح النووي على مسلم.
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
3 መጻሕፍትተጨማሪ (3)
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«عَلَيْكَ بِكَثْرَةِ السُّجُودِ لِلهِ، فَإِنَّكَ لَا تَسْجُدُ لِـِلَّهِ سَجْدَةً إِلَّا رَفَعَكَ اللهُ بِهَا دَرَجَةً، وَحَطَّ عَنْكَ بِهَا خَطِيئَةً»
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالحلقيت ثوبان مولى رسول الله صلى الله عليه وسلم فقلت: أخبرني بعمل أعمله يدخلني الله به الجنة؟ أو قال قلت: بأحب الأعمال إلى الله، فسكت. ثم سألته فسكت. ثم سألته الثالثة فقال: سألت عن ذلك رسول الله صلى الله عليه وسلم، فقال: “عليك بكثرة السجود ل
- محاضرات تعظيم قدر الصلاةمحاضرات في تعظيم قدر الصلاة"عَلَيْكَ بِكَثْرَةِ السُّجُودِ لِلَّهِ، فَإِنَّكَ لَا تَسْجُدُ لِلَّهِ سَجْدَةً، إِلَّا رَفَعَكَ اللهُ بِهَا دَرَجَةً، وَحَطَّ عَنْكَ بِهَا خَطِيئَةً " [41]،