"ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።"
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።"
«مَا أَسْفَلَ مِنَ الكَعْبَيْنِ مِنَ الإِزَارِ فَفِي النَّارِ».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወንዶች ከወገባቸው በታች ያለ አካላቸውን የሚሸፍነውን ልብስ ወይም ሱሪያቸውን ወይም ከዛም ውጪ የሆነውን ልብስ ከቁርጭምጭሚታቸው በታች ዝቅ ከማድረግ አስጠነቀቋቸው። ሽርጡን ከቁርጭምጭሚቱ በታች ዝቅ ያደረገው ሰውዬም ለሰራው ስራ ቅጣት ይሆነው ዘንድ እግሩ እሳት ውስጥ ይሆናል።
ወንዶች ልብስን ከቁርጭምጭሚት በታች ከማርዘም መከልከላቸውንና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል እንደሆነም እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሽርጥን ማስረዘም ከሚለው ጥቅል ውስጥ በአስገዳጅ ምክንያት ያስረዘመ ተነጥሎ ይወጣል። ለምሳሌ ቁርጭምጭሚቱ ላይ ቁስል ወጥቶበት ዝንቦች የሚያውኩትና ከሽርጡ ውጪ ሌላ የሚሸፍንለት ልብስ (ፋሻ) ያላገኘ ሰውን ይመስል።"
ይህ ብይን ወንዶችን ብቻ የሚመለከት ነው። ምክንያቱም ሴቶች ልብሶቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች የክንድ ርዝመት ያህል እንዲለቁ ታዘዋልና።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (7/ 141) (5787).
ተጨማሪ (2)
إرشاد الساري لشرح صحيح البخاري (8/ 418).
ذخيرة العقبى في شرح المجتبى (23/ 76).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
4 መጻሕፍትተጨማሪ (4)
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 4«مَا أَسْفَلَ مِنَ الْكَعْبَيْن مِنَ الإزارِ ففِي النَّارِ».
- قاموس الكبائرموسوعة الكبائر - المجموعة الخامسة«مَا أَسْفَلَ مِنَ الْكَعْبَيْنِ مِنَ الْإِزَارِ فَفِي النَّارِ»
- ما لا يسع أطفال المسلمين جهله«مَا أَسْفَلَ مِنَ الكَعْبَيْنِ مِنَ الإِزَارِ فَفِي النَّارِ»[126]،
- مشروع منهاج زادكزادك 3 طالب نهائي«مَا أَسْفَلَ مِنَ الكَعْبَيْنِ مِنَ الإِزَارِ فَفِي النَّارِ»