Skip to content

የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "

ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡-

“አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "

قَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللهِ، أَنُؤَاخَذُ بِمَا عَمِلْنَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ؟ قَالَ: «مَنْ أَحْسَنَ فِي الْإِسْلَامِ لَمْ يُؤَاخَذْ بِمَا عَمِلَ فِي الْجَاهِلِيَّةِ، وَمَنْ أَسَاءَ فِي الْإِسْلَامِ أُخِذَ بِالْأَوَّلِ وَالْآخِرِ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት አብራሩ። እስልምናውን አሳምሮ፣ እውነተኛና ሙኽሊስ (ያጠራ) ሆኖ የሰለመ ሰው ከመስለሙ በፊት በሠራው ወንጀል አይጠየቅም። ወደ እስልምና ከገባ በኋላ ሙናፊቅ በመሆን ወይም ከእምነቱ በመውጣት መጥፎ የሠራ ግን በክህደት ዘመኑም ሆነ በእስልምና ዘመኑ ስለ ሠራው ሥራ ይጠየቃል።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በጃሂሊያ ዘመን ለሰሩት ስራ የሰጡት ትኩረትና ፍርሃታቸውን እንረዳለን።

በእስልምና ላይ መፅናት መበረታታቱን እንረዳለን።

ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት እንረዳለን። እሱም ያለፈውን መጥፎ ስራዎች ማስማሩ ነው።

ከእስልምና የወጣና ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቀደም ብሎ ከመስለሙ በፊት ስለ ሠራቸው ሁሉ ሥራዎችና በእስልምና ውስጥም ስለ ሰራቸው ሁሉ ወንጀሎች ይጠየቃል።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (9/ 14) (6921).

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 111) (120).

ተጨማሪ (3)

مشارق الأنوار على صحاح الآثار (2/229).

الكواكب الدراري (24/43).

عمدة القاري شرح صحيح البخاري (24/ 76).