Skip to content

"ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን

ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦

"ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"

أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ إِذَا أَوَى إِلَى فِرَاشِهِ كُلَّ لَيْلَةٍ جَمَعَ كَفَّيْهِ، ثُمَّ نَفَثَ فِيهِمَا فَقَرَأَ فِيهِمَا: {قُلْ هُوَ اللهُ أَحَدٌ}، وَ{قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ}، وَ{قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ}، ثُمَّ يَمْسَحُ بِهِمَا مَا اسْتَطَاعَ مِنْ جَسَدِهِ، يَبْدَأُ بِهِمَا عَلَى رَأْسِهِ وَوَجْهِهِ وَمَا أَقْبَلَ مِنْ جَسَدِهِ، يَفْعَلُ ذَلِكَ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ.

ቡኻሪ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያደርግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በአፋቸው እየነፉበት ሶስት ምእራፎች ያነቡበታል። {ሱረቱል ኢኽላስ}ን፣ {ሰረቱል ፈለቅ}ን፣ {ሱረቱ አንናስ}ን ከዚያም የቻሉትን ያህል የሰውነታቸውን ክፍል ከጭንቅላታቸው፣ ከፊታቸውና ከሰውነታቸው የፊትለፊት ክፍል በመጀመር በመዳፋቸው ያብሱታል። ይህንንም ድርጊት ሦስት ጊዜ ይደጋግሙታል።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ከመተኛት በፊት የኢኽላስን ምእራፍና ሙዐወዘተይንን መቅራትና ምራቅ የቀላቀለን ትንፋሽ በመንፋት የተቻለውን ያህል የሰውነትን ክፍል ማበስ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (6/ 190) (5017).

(7/ 133) (5748).

ተጨማሪ (5)

الكاشف عن حقائق السُّنن (5/1651).

عمدة القاري شرح صحيح البخاري (20/ 35).

التوضيح لشرح الجامع الصحيح ( 24/ 91).

النهاية في غريب الحديث والأثر (ص 929).

شرح سنن أبي داود لابن رسلان (19/268).