"የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ
ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)
«سَيِّدُ الِاسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لاَ إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي، فَإِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ» قَالَ: «وَمَنْ قَالَهَا مِنَ النَّهَارِ مُوقِنًا بِهَا، فَمَاتَ مِنْ يَوْمِهِ قَبْلَ أَنْ يُمْسِيَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ، وَمَنْ قَالَهَا مِنَ اللَّيْلِ وَهُوَ مُوقِنٌ بِهَا، فَمَاتَ قَبْلَ أَنْ يُصْبِحَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ».
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምህረት የሚጠየቅበት የተለያዩ ቃላቶች እንዳሉና በላጩና ትልቁ አንድ ባሪያ እንዲህ ብሎ መጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ: "አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረህኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።) በቅድሚያ ባሪያው የአላህን ብቸኝነት ያረጋግጣል። አላህ ፈጣሪው፣ ምንም አጋር ሳይኖረው የሚያመልከው መሆኑን፤ ጥራት ለተገባው አላህ የገባውን በርሱ የማመንና ለርሱ ታዛዥ የመሆንን ቃልኪዳን በአቅሙ ልክ እንደሚወጣ ያረጋግጣል። በአቅሙ ልክ ቃሉን እንደሚወጣ የሚያረጋግጠውም አንድ ባሪያ ምንም ያክል በአምልኮ ላይ ቢቆም አላህ ያዘዘውን ሁሉ መፈፀም ስለማይችል ነው። ለተዋለለት ፀጋ የሚገባውን ምስጋናም ማቅረብ አይችልም። ወደ አላህም ይጠጋል፣ በርሱም ይጠበቃል፣ ባሪያ ከሰራው ክፋት መጠበቂያው አላህ ነውና። አላህ ለርሱ የዋለለትን ፀጋም በታዛዥነት ለርሱ ያረጋግጣል፤ እውቅናንም ይሰጣል። ወደ ነፍሱ በመመለስም ወንጀሉና ኃጢአቱን ያረጋግጣል፤ ያምናልም። በዚህ መልኩ ወደ አላህ ከተቃረበ በኋላ ጌታው እንዲምረው፣ ወንጀሎቹን እንዲሸሽግለት፣ በይቅር ባይነቱ፣ በችሮታውና እዝነቱ ከወንጀሎቹ እንዲጠብቀውም ዱዓ ያደርጋል። ምክንያቱም ከአላህ በቀርም ወንጀሎችን የሚምር የለምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ዱዓ ከንጋትና ምሽት ውዳሴዎች መካከል መሆኗንና በቀኑ መጀመሪያ ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ ወደ መግቢያዋ ዘንበል እስክትል ድረስ ባለው ወቅት ላይ በእርግጠኝነት፣ መልዕክቷን በማሰብ አምኖባት ካለ በኃላ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን ተናገሩ። በምሽትም ወቅት እርሱም ፀሀይ ከገባችበት አንስቶ ጎህ እስኪወጣ ድረስ ያለ ሰውና ከመንጋቱም በፊት የሞተ ጀነት ይገባል።
...:
ምህረትን የመጠየቂያ ቃላቶች የተለያዩ ሲሆኑ ከፊሉም ከከፊሉ ይበላለጣል።
አንድ ባሪያ በዚህ ዱዓ አላህን ለመለመን መጓጓት ይገባዋል። ምክንያቱም የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ ነውና።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 67) (6306).
ተጨማሪ (6)
توضيح الأحكام من بلوغ المرام.
لعبد الله البسام (7/ 562).
منحة العلام في شرح بلوغ المرام.
لعبد الله الفوزان (10/ 435).
فتح ذي الجلال والإكرام.
لابن عثيمين (6/ 486).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
11 መጻሕፍት- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمአላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረኸኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔም በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህና በተስፋ ቃልህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በእኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ [107]፣ ኃጢአቴንም አምናለሁና ማረኝ! እነሆ ከአንተ በቀር ኃጢአቶችን የሚምር ማንም የለምና።) [108]
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمአላሁምመ አንተ ረቢ ላ ኢላሀ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ፣ ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መስተጠዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሰነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈኢነሁ ላ የግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ
ተጨማሪ (9)
- الذكر والدعاء والعلاج بالرقي من الكتاب والسنة"سيد الاستغفار أن تقول: اللهم أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتني وأنا عبدك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعت. أعوذ بك من شر ما صنعت، أبوء لك بنعمتك علي، وأبوء بذنبي. فاغفر لي فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت". قال: ومن قالها من النهار موقناً بها فات م
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“سيد الاستغفار أن تقول: (اللهم أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتني وأنا عبدك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعت، أعوذ بك من شر ما صنعت، أبوء لك بنعمتك علي، وأبوء لك بذنبي فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت)
- تحفة الأخيار تحفة الأخيار (ببيان جملة نافعة مما ورد في الكتاب والسنة من الأدعية والأذكار)«سَيِّدُ الاِسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَي
- تحفة الأخيار تحفة الأخيار (ببيان جملة نافعة مما ورد في الكتاب والسنة من الأدعية والأذكار)«سَيِّدُ الاِسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَي
- تطبيق القرآن والأذكارأذكار الصباح والمساء((اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ[9] لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ
- رسالة في الأذكار1«سَيِّدُ الِاسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَ
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 8«سَيِّدُ الاسْتِغْفَارِ أَنْ يَقُولَ الْعَبْدُ: اللهم أَنْتَ رَبّي، لا إلهَ إلَّا أَنْتَ خَلَقْتَني وَأَنا عَبْدُكَ، وأَنا عَلىٰ عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ ما اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أبوءُ لَكَ بِنــعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأ
- ما لا يسع أطفال المسلمين جهله٣. «اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْف
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «سَيِّدُ الاِسْتِغَفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي، لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَ