Skip to content

"ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

"ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"

«لَا تَسُبُّوا الْأَمْوَاتَ، فَإِنَّهُمْ قَدْ أَفْضَوْا إِلَى مَا قَدَّمُوا».

ቡኻሪ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሟቾችን መሳደብና ክብራቸውን መንካት ክልክል መሆኑን አብራሩ። ከእኩይ ስነ ምግባሮችም የሚመደብ እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ስድብ በህይወት ያሉ ሰዎችን ከመጉዳት በዘለለ ለነርሱ የማይደርሳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ እነርሱ ወዳስቀደሙት መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ደርሰዋልና።

የቃላት ፍቺ

أفضوا إلى ما قدموا : صاروا إلى ما قدموا من أعمالهم.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ሐዱሡ ሟቾችን መሳደብ ክልክል መሆኑን ይጠቁማል።

ሟቾችን ከመሳደብ መታቀብ የህያው ሰዎችን ጥቅምም የማህበረሰቡንም ሰላም ከመጣላትና ከመናቆር ይጠብቃል።

ሟቾችን ከመሳደብ የመከልከሉ ጥበብ ወዳስቀደሙት ስራ ስለደረሱ መስደቡ ከንቱ ስለሆነና በተጨማሪ የህያው ቅርብ ዘመዶቹን ስለሚያውክ ነው።

የሰው ልጅ ጥቅም የሌለውን ነገር መናገር አይገባውም።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (2/ 104) (1393).

ተጨማሪ (6)

فتح ذي الجلال والاكرام بشرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (2/ 631).

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (4/ 385).

توضيح الأحكام من بلوغ المرام.

للبسام (3/ 277).