Skip to content

"ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።"

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

"ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።"

«لَا يَحِلُّ لِرَجُلٍ أَنْ يَهْجُرَ أَخَاهُ فَوْقَ ثَلَاثِ لَيَالٍ، يَلْتَقِيَانِ، فَيُعْرِضُ هَذَا وَيُعْرِضُ هَذَا، وَخَيْرُهُمَا الَّذِي يَبْدَأُ بِالسَّلَامِ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን አንዱ ሌላኛውን በሚያገኘው ጊዜ ሰላምታም ሳይሰጠውና ሳያናግረው ከሶስት ሌሊቶች በላይ ማኩረፍን ከለከሉ። ከነዚህ ሁለት ጠበኞች መካከል በላጩ ኩርፊያውን ለማስወገድ የሚሞክርና ሰላምታ የሚጀምረው ነው። እዚህ ሐዲስ ውስጥ ኩርፊያ በማለት የተፈለገው በነፍሱ ፍላጎቶች ያኮረፈ ከሆነ ነው። ወንጀለኞችን፣ የቢድዓ ባለቤቶችንና መጥፎ ጓደኞችን የመሰሉ ሰዎችን ለአላህ ሀቅ ብሎ ማኩረፍ ከሆነ ግን በወቅት ሳይሆን የሚገደበው ኩርፊያው በሚያመጣው ጥቅምና ያለባቸው ችግር በመወገዱ ላይ ነው የሚገደበው።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ለማስጠበቅ ሲባል ለሶስት ቀንና ከዛ በታች ማኩረፍ እንደተፈቀደ እንረዳለን። ለሶስት ቀናት ማኩረፉም ይቅር የተባለው ይህንኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ለማስተናገድ ሲባል ነው።

ሰላምታ ነፍሶች ውስጥ ያለን አለመግባባት ማስወገዱና የመዋደድ ምልክትም በመሆኑ የሰላምታን ደረጃ ያስረዳናል።

ኢስላም በወንድማማችነት ላይና በአማኞቹ አንድነት ዙሪያ መጓጓቱን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 21) (6077).

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 1984) (2560).

ተጨማሪ (6)

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (10/ 111).

فتح ذي الجلال والإكرام بشرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (6/ 293).

توضيح الأحكام من بلوغ المرام.

للبسام (7/ 339).