"መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።"
ከአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።"
«لاَ تَدْخُلُ المَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ كَلْبٌ وَلاَ صُورَةٌ».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእዝነት መላዕክቶች ውሻና ነፍስ ያላቸው የፍጡራን ስዕል ወዳለበት ቤት እንደማይገቡ ተናገሩ። ይህም ነፍስ ያለበት ምሥል አስከፊ ወንጀል ስለሆነ፤ ከአላህ አፈጣጠር ጋር መፎካከር ስለሆነ፤ የሽርክ መዳረሻም ስለሆነ፤ አንዳንዶቹ ምሥሎችም ከአላህ ውጪ የሚመለኩ ምሥሎች ስለሆኑ ነው። ውሻ ያለበት ቤት ከመግባት የመቆጠባቸው ምክንያት ደግሞ: በብዛት ነጃሳ ስለሚመገብ፤ አንዳንዶቹም ሸይጧን ተብለው ስለተጠሩ ነው። መላዕክት ደግሞ የሸይጧን ተቃራኒ ናቸው። በተጨማሪ የውሻ ሽታ አፀያፊ ስለሆነ ነው። መላዕክት ደሞ መጥፎ ሽታን ይጠላሉ። ስለዚህ ውሻን ማሳደግ ተከለከለ። የሚያሳድግ ሰውም የእዝነት መላዕክት ቤቱ ባለመግባታቸው፤ ለቤቱ ዱዓእ ባለማድረጋቸው፤ ለርሱ ምህረት ባለመጠየቃቸው፤ ለርሱና ለቤቱ በረከት ባለመጠየቃቸው፤ የሸይጧንን ጉዳት ከርሱ ላይ ባለመከላከላቸው ተቀጣ።
የአደን ውሻ ወይም የከብት ጠባቂ የሆነ ውሻ ወይም የአዝርዕት ጠባቂ የሆነ ውሻ ካልሆነ በቀር ውሻን ማሳደግ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ስዕል ማስቀመጥ መላዕክት የሚሸሹት ከሆኑ ቆሻሻ ጉዳዮች አንዱ ነው። በአንድ ስፍራ ስዕል መኖሩ እዝነትን እንድንነፈግ ምክንያት ይሆነናል። ውሻም ልክ እንደዚሁ ነው።
ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት ውስጥ የማይገቡት መላዕክቶች የእዝነት መላዕክቶች ናቸው እንጂ ስራን የሚመዘግቡና ሌሎች እንደ መልዐከ ሞት የመሰሉ የስራ ድርሻ ያላቸው መላዕክቶች ግን ሁሉም ቤት ይገባሉ።
ግድግዳና ሌሎች ነገሮች ላይ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ስዕላቸውን ማንጠልጠል ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ኸጧቢ እንዲህ ብለዋል: «መላዕክት ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት የማይገቡት ማስቀመጡ ክልክል የሆኑ ውሻዎችንና ስዕሎችን ነው። ክልክል ያልሆኑ የአደን ውሻ፣ የአዝርዕትና የከብቶች ጠባቂ የሆኑ ውሻዎችን እንዲሁም ምንጣፍ ላይ፣ ትራስ ላይና የመሳሰሉት ላይ የሚኖሩ ስዕሎች ግን በነርሱ ምክንያት መላዕክት ከመግባት አይቆጠቡም።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (4/ 130) (3322).
ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1665) (2106).
(3/ 1664) (2104).
ተጨማሪ (12)
نزهة المتقين.
جمعٌ من المشايخ (2/ 1153).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (20/ 29).
بهجة الناظرين.
لسليم الهلالي (3/ 185).
فتح الباري شرح صحيح البخاري.
لأحمد العسقلاني (10/ 381).
تحفة الأحوذي بشرح جامع الترمذي.
للمباركفوري (8/ 72).
لقاء الباب المفتوح.
لابن عثيمين (2/ 42 بترقيم الشاملة آليا).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
6 መጻሕፍትተጨማሪ (6)
- اللآلئ المضيئةعَنْ أَبِي طَلْحَةَ رضي الله عنه ، عَنِ النَّبِيِّ ﷺ قَالَ: “ لَا تَدْخُلُ الْمَلَائِكَةُ بَيْتًا فِيهِ كَلْبٌ وَلَا صُورَةُ تَمَاثِيلَ “.
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 8«لا تدخُلُ الملائكَةُ بيتاً فيه كلبٌ ولا صُورةٌ».
- قاموس الكبائر موسوعة الكبائر - المجموعة الأولى«لَا تَدْخُلُ المَلَائِكَةُ بَيْتًا فِيهِ كَلْبٌ وَلَا صُورَةٌ» [161].
- قاموس الكبائر«لَا تَدْخُلُ المَلَائِكَةُ بَيْتًا فِيهِ كَلْبٌ وَلَا صُورَةٌ» [161].
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (3)، والسيرة النبوية (3)التربية الإٍسلامية -3- «لا تدخل الملائكة بيتا فيه كلب ولا صورة»
- محرمات استهان بها كثير من الناسلا تدخل الملائكة بيتا فيه كلب ولا تصاوير