"የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'"
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'" በቡኻሪ ዘገባ ደግሞ "ህፃን ለትልቅ ሰላምታን ያቅርብ፤ ተጓዥ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች ለብዙ ሰዎች ሰላምታን ያቅርቡ።"
«يُسَلِّمُ الرَّاكِبُ عَلَى المَاشِي، وَالمَاشِي عَلَى القَاعِدِ، وَالقَلِيلُ عَلَى الكَثِيرِ». وَلِلبُخَارِي: «يُسَلِّمُ الصَّغِيرُ عَلَى الكَبِيرِ، وَالمَارُّ عَلَى القَاعِدِ، وَالقَلِيلُ عَلَى الكَثِيرِ».
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰዎች መካከል "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ" የሚለውን ሰላምታን የማቅረብ ስነ-ስርዓትን ጠቆሙ። ይኸውም ህፃን ለትልቅ፣ ጋላቢ ለእግረኛ፣ እግረኛ ለተቀማጭ፣ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በብዙዎቹ ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።
ሐዲሥ ላይ በመጣው መልኩ ሰላምታን ማቅረብ እንደሚወደድ እንረዳለን። ነገር ግን እግረኛ ለጋላቢ ወይም ከዚህም ውጪ ሐዲሡ ላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒው ሰላምታ ቢያቀርብ ከበላጩና ከተሻለው ተቃራኒ ቢሆንም ይፈቀዳል።
በሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው አፈፃፀም መልኩ ሰላምታን ማስፋፋት ውዴታንና ትስስርን ከሚያመጡ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
በሐዲሡ ላይ የተጠቀሱት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ ከሆኑ በላጩ ሰው ሰላምታውን የሚጀምረው ነው።
የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን ሁሉ በማብራራት ረገድ የሸሪዓን ምሉዕነት እንረዳለን።
የሰላምታን ስነ-ስርዓት ማስተማርና ለሁሉም የሚገባውን ሐቅ (መብት) መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 52) (6232).
ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 1703) (2160).
ተጨማሪ (11)
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (11/ 280).
بهجة الناظرين.
تأليف: سليم الهلالي (2/ 137).
نزهة المتقين.
مجموعة من الباحثين (1/ 666).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (4/ 407).
منار القاري.
لحمزة قاسم (5/ 257).
الأدب النبوي (ص159).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
4 መጻሕፍትተጨማሪ (4)
- الحقيقة المُبْهِرَة في العلاقة بين الإسلام والإنسان(يسلم الصغير على الكبير، والمار على القاعد، والقليل على الكثير)[224].
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 5«يُسَلِّمُ الرَّاكبُ عَلَىٰ المَاشي، والمَاشي عَلَىٰ القَاعد، والقليلُ عَلَىٰ الكَثير».
- ما لا يسع أطفال المسلمين جهله«يُسَلِّمُ الرَّاكِبُ عَلَى المَاشِي، وَالمَاشِي عَلَى القَاعِدِ، وَالقَلِيلُ عَلَى الكَثِيرِ»[153].
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «يُسَلِّمُ الرَّاكِبُ عَلَى الْمَاشِي، وَالْمَاشِي عَلَى الْقَاعِدِ، وَالْقَلِيلُ عَلَى الْكَثِيرِ»