"የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች… "
ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች… "
«مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الكَهْفِ، عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ». وفي رواية: «مِنْ آخِرِ سُورَةِ الكَهْف».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን በቀልቡ የሸመደደ ሰው በመጨረሻ ዘመን መጥቶ ለራሱ ጌትነትን ከሚሞግተው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ይጠበቃል ብለው ተናገሩ። የደጃል ፈተና አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ትንሳኤ እስኪቆም ድረስ ምድር ከምታስተናግደው ፈተና ሁሉ ከባዱ ፈተና ነው። ተከታዮቹን ሊፈትንበት ዘንድ ከተለምዶ የወጡ አንዳንድ ተአምራት አላህ አስመችቶለታል። እነዚህን አንቀጾች መቅራት ከርሱ የሚጠብቀው ምክንያትም የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾች ውስጥ ደጃል ሰዎችን ከሚፈትናቸው ፈተናዎች የበለጠ ትላልቅ ተአምራትና አስደናቂዎች ስለሚገኙ ነው። እነዚህን አንቀጾች ያስተነተነ በደጃል አይፈተንም። በሌላ ዘገባም: "ከምዕራፉ መጨረሻ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ማለትም {እነዚያ የካዱት ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን (የማያስቆጣኝ አድርገው) አሰቡን .....} ከሚለው ጀምሮ ነው።
የሱረቱል ከህፍ ትሩፋት መገለፁን እንረዳለን። ይህም መክፈቻዎቿ ወይም መጨረሻዎቿ ከደጃል ፈተና መጠበቃቸው ነው።
የደጃል ጉዳይ መነገሩና ከርሱ መጠበቂያም መነገሩን እንረዳለን።
ሱረቱል ከህፍን ሙሉውን በቃል በመሸምደድ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህ ካቃተው ግን ከመጀመሪያውና ከመጨረሻው አስር አንቀጾችን ይሸምድድ።
ስለዚህ ምክንያትም ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: «በምክንያቱ ዙሪያ አስሩ አንቀጾች የዋሻው ሰዎች ታሪክ ውስጥ ያሉ ተአምራትን ስላካተቱ ነው። ቆም ብሎ ስለነሱ ያስተነተነ ሰው የደጃል ጉዳይ እንግዳ አይሆንበትምም አያስደነግጠውምም። ስለዚህ በርሱ ፈተና ውስጥ አይወድቁም ተብሏል። {ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱ ቅጣት ሊያስፈራራበት} የሚለው የቁርአን አንቀፅ ስላለበት መከራና ችግርን ከርሱ ዘንድ ብቻ እንደሆነ መገደቡን በመያዝ ነውም ተብሏል። ይህም ደጃል አምላክነትንና የበላይነትን ከመሞገቱ ጋር ፈተናው ታላቅ መሆኑን የሚገጥም ነው። ስለዚህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የደጃልን ጉዳይ አከበዱት፤ ከርሱም አስጠነቀቁ፤ ከፈተናውም ተጠበቁ። ስለዚህ የሐዲሡ ሀሳብ የሚሆነው እነዚህን አስር አንቀጾች ያነበበ፣ ያስተነተነ፣ በየትርጉሙ ቆም እያለ ያገናዘበ ሰው ደጃልን ይጠነቀቃልም። ከርሱም ደህና ይሆናል ማለት ነው።»
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 555) (809).
ተጨማሪ (11)
بهجة الناظرين.
لسليم الهلالي (2/ 243).
شرح النووي على مسلم (6/ 92).
فيض القدير شرح الجامع الصغير.
لعبدالرؤوف المناوي (6/ 119).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (13/ 115).
مرقاة المفاتيح شرح مشكاة المصابيح.
لملا القاري (4/ 1465).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمصطفى الخن (2/ 760).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
5 መጻሕፍትተጨማሪ (4)
- الذكر والدعاء والعلاج بالرقي من الكتاب والسنة"من حفظ عشر آيات من أول سورة الكهف عُصِمَ من الدجال" .
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“من حفظ عشر آيات من أول سورة الكهف عصم من الدجال”.
- النفحات المكية في تفسير كتاب رب البرية الجزء الخامس عشر«مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الْكَهْفِ، عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ»[1].
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 5«مَن حفظَ عشْرَ آياتٍ مِن أوَّلِ سورةِ الكَهْفِ عُصمَ مِنَ الدَّجَّالِ». وفي رواية: «مِن آخرِ سورةِ الكَهْفِ».