Skip to content

"'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦

"'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?' ሶሐቦችም 'ከእድፉ አንዳችም አያስቀርም።' አሉ። እርሳቸውም 'ይህ የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው። አላህ በሶላት ወንጀሎችን ያብሳል።' አሉ።"

«أَرَأَيْتُمْ لَوْ أَنَّ نَهَرًا بِبَابِ أَحَدِكُمْ يَغْتَسِلُ فِيهِ كُلَّ يَوْمٍ خَمْسًا، مَا تَقُولُ ذَلِكَ يُبْقِي مِنْ دَرَنِهِ؟» قَالُوا: لَا يُبْقِي مِنْ دَرَنِهِ شَيْئًا، قَالَ: «فَذَلِكَ مِثْلُ الصَّلَوَاتِ الخَمْسِ، يَمْحُو اللَّهُ بِهِ الخَطَايَا».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጧትም በማታም የሚሰገዱትን አምስቱ ሶላቶች ትናንሽ ወንጀሎችንና ኃጢአቶችን ማስማራቸውና ማስወገዳቸውን፤ አንድ ሰው በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት በሆነ በሩ ላይ እንዳለ ወንዝ መሰሉት። ከእድፉና ቆሻሻው አንዳችም አይቀርምና።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ይህ ትሩፋት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ በማስማር የተገደበ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

አምስቱን ሶላቶች የመፈፀምና የእነርሱን መስፈርቶች፣ ማእዘናቶች፣ ግዴታዎችና ሱናዎችን የመጠባበቅን ትሩፋት እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 112) (528).

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 462) (667).

(1/ 282).

ተጨማሪ (7)

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.

مجموعة من الباحثين (2/ 773).

تطريز رياض الصالحين.

لفيصل آل مبارك (ص610).

المعجم الوسيط.

النهاية في غريب الحديث والأثر.

لابن الأثير (2/ 115).