Skip to content

"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"

ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"

«مَنْ حَلَفَ بِالْأَمَانَةِ فَلَيْسَ مِنَّا».

አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአደራ ከመማል ከለከሉም አስጠነቀቁም። ይህን ድርጊት የፈፀመም ከኛ አይደለም አሉ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ከአላህ ውጪ መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ከዚህም መካከል በአደራ መማል አንዱ ነው። ይህም ከትንሹ ሺርክ መካከል ነው።

አማና የምትለዋ ቃል ትእዛዝን፣ አምልኮን፣ አደራን፣ ገንዘብንና ደህንነትን የሚጠቀልል የወል ስም ነው።

መሃላ በአላህ ወይም ከስሞቹ መካከል በአንድ ስሙ ወይም ከባህሪያቶቹ መካከል በአንድ ባህሪው ካልሆነ በቀር አይታሰርም።

ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ክልከላ የመጣው እርሳቸው በአላህና በባህሪያቱ እንዲምል ስላዘዙ ይመስላል። አደራ ደሞ ከአላህ ባህሪያቶች መካከል ሳይሆን ከትእዛዞቹ መካከል አንድ ትእዛዙ፣ ከግዴታዎቹ መካከል አንዱ ግዴታው ነው። ከዚህ የተከለከሉትም በርሷ መካከልና በአላህ ስምና ባህሪያት መካከል እኩል ማድረግ ስለሚሆን ነው።"

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (5/ 155) (3253).

ሙስነድ አሕመድ (38/ 82) (22980).

ተጨማሪ (12)

نزهة المتقين.

لمجموعة من الباحثين (2/ 1166).

بهجة الناظرين.

لسليم الهلالي (3/ 201).

مشكاة المصابيح.

للتبريزي (2/ 1020).

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (6/ 452).

معالم السنن.

للخطابي (4/ 46).

سبل السلام.

الصنعاني (2/ 550 ).