Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 52 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'መጠናቸው በነዚህ ልክ ያሉ ጠጠሮችን ወርውሩ!' አሉ። ቀጥለውም 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።"
ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ፣ ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።"
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
"የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።"
ሶሒሕ ነው። ኢማም አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
"የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይ እና ነሳኢይ ዘግበውታል
"ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
"ጥፍጥናን ቆራጩን ማስታወስ አብዙ።" ሞትን ማለታቸው ነው።
ሐሰን ነው። ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"
ሐሰን ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ "አልኩብራ" ውስጥ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል