Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 51 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት። ኩራት እንጂ ሌላ አልከለከለውም። ሰለማ እንዲህ አለ '(ከዛ በኃላ) እጁን ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።' "
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።