Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 87 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (46)
"አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።»
ሶሒሕ ነው። ኢብን ኹዘይማ፣ ዳረቁጥኒይ እና በይሀቂይ ዘግበውታል
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። አንድ ሰውዬም መስጂድ ገባና ሰገደ። ነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱና እንዲህ አሉት "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" ቀደም ብሎ እንደሰገደው ለመስገድ ተመለሰ። ቀጥሎም በመምጣት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" እያሉት ሶስት ጊዜ ተመላለሰ። እርሱም "ያ በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አላቸው። እርሳቸውም "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም ከቁርአን (ፋቲሓንና) የገራልህን ቅራ! ከዚያም በተረጋጋ ሁኔታ አጎንብስ፤ ከዚያም ቀጥብለህ በቆምክበት እስክትረጋጋ ድረስ ተነሳ፤ ከዚያም በሱጁድህ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ አድርግ፤ ከዚያም ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ተነሳ! በሁሉም የሶላትህ ክፍልም ይህንን ፈፅም።" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጣዕረ ሞት ባጋጠማቸው ጊዜ አብዝተው ይመክሩት የነበሩት ምክር " ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ! ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!" የሚል ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይህን ምክር ከልባቸው ጉሮሯቸው ድረስ እስኪተናነቃቸው ደጋግመው ይሉት ነበር። ነገር ግን ምላሳቸው ልታወጣው ይሳናቸው ነበር።"
ሶሒሕ ነው። رواه النسائي في السنن الكبرى وابن ماجه
«ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ። እነርሱም ከዙህር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዙህር በኋላም ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻእ በኋላም ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከሱብሒ ሶላት በፊት ሁለት ረከዓ ናቸው። የሱብሒ ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የማይገባባት ሰአት ነበረች። ስለሰአቲቱም ሙአዚኑ አዛን ያለ ጊዜና ጎህ የወጣ ጊዜ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ እንደነበር ሐፍሷ ነገረችኝ።" በሌላ ዘገባ ደግሞ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። በሁሉም ዘገባዎቹ ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።