Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 12 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።
አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሱብሒን አሰገዱንና "እከሌ አብሮን ሰግዷልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። እርሳቸውም "እከሌስ ተሳትፏልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። እርሳቸውም "እነዚህ ሁለት ሶላቶች በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላት ናቸው። በነዚህ ሶላቶች ያለውን ምንዳ ብታውቁ ኖሮ በጉልበታችሁ እየዳኻችሁም ቢሆን ትመጡ ነበር። የመጀመሪያው ሰልፍ በመላዕክት ሰልፍ አምሳያ ነው። በርሱ የሚገኘውን ደረጃ ብታውቁ ኖሮ ትቻኮሉለት ነበር። ሰውዬው ከሌላ ሰው ጋር የሚሰግደው ሶላት ብቻውን ከሚሰግደው ሶላት የተሻለ ነው። ከሁለት ሰዎች ጋር የሚሰግደው ሶላት ከአንድ ሰው ጋር ከሚሰግደው ሶላት የተሻለ ነው። ህብረቱ በበዛበት ልክ አላህ ዘንድም እጅግ ተወዳጅ ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና አሕመድ ዘግበውታል
"የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።
"ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።"
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
"ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።"
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አሕመድ ዘግበውታል
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና አሕመድ ዘግበውታል