"የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"
«يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الْآخِرُ، يَقُولُ: «مَنْ يَدْعُونِي فَأَسْتَجِيبَ لَهُ؟ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ؟ مَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ؟».
የጠራውና ከፍ ያለው አላህ በሁሉም ሌሊት የሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በመውረድ እርሱ ለለመነው ተቀባይ ለጠየቀው ሰጪ ነውና ባሮቹ እንዲለምኑት እንደሚያነሳሳ፤ የሚፈልጉትን እንዲጠይቁት እንደሚያነሳሳ፤ እርሱ ለአማኝ ባሮቹ መሀሪ ነውና ለወንጀሎቻቸውም ከርሱ ምህረትን እንዲፈልጉ እንደሚያበረታታቸው ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ገለፁ።
የሌሊቱ የመጨረሻው ሲሶ ትሩፋቱንና በዚህ ወቅት ሶላት መስገድ ፣ ዱዓእ ማድረግና ምህረትን መፈለግ ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
አንድ ሰው ይህንን ሐዲሥ በሚሰማበት ጊዜ ዱዓእ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅትን በመሸመት ላይ እጅግ የሚጓጓ ሊሆን ይገባል።
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 521) (758).
ተጨማሪ (3)
صحيح البخاري صحيح البخاري (2/ 53) (1145).
الإفصاح عن معاني الصحاح.
ليحيى بن هبيرة (6/ 195).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
3 መጻሕፍትተጨማሪ (3)
- عقيدة أهل السنة والجماعة«من يدعوني فأستجيب له؟ من يسألني فأعطيه؟ من يستغفرني فأغفر له؟».
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (3)، والسيرة النبوية (3)التربية الإٍسلامية -3- «ينزل ربُّنا تبارك وتعالى كلَّ ليلةٍ إلى السماءِ الدنيا حين يبقى ثلثُ الليلِ الآخِرُ، يقول: من يدْعُوني فأستجيبَ له؟ من يسألُني فأعطيَه؟ من يستغفرُني فأغفرَ له»
- موسوعة الإيمان«يَنْزِلُ رَبُّنَا تبارك وتعالى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الآخِرُ، يَقُولُ: مَنْ يَدْعُونِي فَأَسْتَجِيبَ لَهُ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ، مَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ»