በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"
ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"
«مَنْ شَهِدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، وَأَنَّ عِيسَى عَبْدُ اللهِ وَرَسُولُهُ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَى مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ، وَالْجَنَّةُ حَقٌّ، وَالنَّارُ حَقٌّ، أَدْخَلَهُ اللهُ الْجَنَّةَ عَلَى مَا كَانَ مِنَ الْعَمَلِ».
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያለው: የተውሒድን ቃል ትርጉሙን አውቆ የሚያስፈርደውንም በመስራት የተናገረ ሰው፤ እንዲሁም በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባርነትና መልክተኝነት የመሰከረ፤ የዒሳን ባርነትና መልክተኝነት ያመነ፤ አላህ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደፈጠራቸውና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነፍስ እንደሆኑም የመሰከረ፤ አይሁዶች ወደርሷ ካስጠጉት ዘለፋም እናቱን መርየምን ያጠራ፤ መኖራቸውንና የአላህ ፀጋና ቅጣቱ መሆናቸውን ከማመን ጋር ጀነትም እውነት መሆኑን፣ እሳትም እውነት መሆናቸውን ያመነ ሰው በአምልኮዎች ላይ ያጓደለና ወንጀሎችም ያሉበት ቢሆን እንኳ በዚህ እምነት ላይ ከሞተ መመለሻው ወደ ጀነት ነው።
لا إله إلا الله: لا معبود بحق إلا الله.
ألقاها إلى مريم: أرسل بها جبريل إليها فنفخ فيها من روحه بإذن الله عز وجل.
ከፍ ያለው አላህ የመርየም ልጅ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ ብቻ ያለ አባት ነው የፈጠራቸው።
ዒሳና ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንና) የአላህ ባሪያዎችና መልዕክተኛዎች በመሆናቸው የማይስተባበሉ መልክተኞችና የማይመለኩ ባሪያዎች መሆናቸውን እንረዳለን።
የተውሒድን ትሩፋትና ወንጀሎችን እንደሚያስምር እንረዳለን። ተውሒድን የያዘ ሰውም ከፊል ወንጀል ላይ ቢወድቅ እንኳ መመለሻው ጀነት ነው።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (4/ 165) (3435).
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 57) (28).
ተጨማሪ (4)
الملخص في شرح كتاب التوحيد.
لصالح الفوزان (ص25).
الجديد في شرح كتاب التوحيد.
لمحمد القرعاوي (ص36).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
9 መጻሕፍት- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلم«ከአላህ በቀር በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም»
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمላ ኢላሀ ኢለላህ
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمከአላህ በቀር በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም።
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمላ ኢላሀ ኢለላህ
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلم«ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም!» [291].
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمላ ኢላሃ ኢለላህ
- የሙስሊም ምሽግ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዚክሮችحصن المسلمላ ኢላሀ ኢለላህ
ተጨማሪ (2)
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 3«مَنْ شَهِدَ أَنْ لا إلهَ إلَّا الله وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّداً عَبْدُهُ وَرسُولُهُ، وَأَنَّ عِيسَىٰ عَبْدُ الله وَرَسُولُهُ، وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إلىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ، وَأنَّ الجَنَّةَ حَقٌّ وَأنَّ النَّارَ حَ
- مادة العقيدة الإسلامية(من شهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأن محمدًا عبده ورسوله، وأن عيسى عبد الله ورسوله وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه، والجنة حق، والنار حق، أدخله الله الجنة على ما كان من العمل).