"ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"
«لَيْسَ شَيْءٌ أَكْرَمَ عَلَى اللهِ تَعَالَى مِنَ الدُّعَاءِ».
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ስለያዘ ነው።
...:
የዱዓእን ትሩፋት እንረዳለን። አላህን የለመነ ሰው አላህን እያላቀ ነው። የሌለው አይከጀልምና ጥራት የተገባው አምላክ እጅግ የተብቃቃ መሆኑን እየመሰከረ ነው። ደንቆሮ አይለመንምና እጅግ ሰሚ መሆኑን፣ ስስታም አይለመንምና ቸር መሆኑን፣ ልበደረቅ አይለመንምና አዛኝ መሆኑን፣ ደካማ አይለመንምና ቻይ መሆኑን፣ ሩቅ ያለ አይሰማምና ቅርብ መሆኑን እና ሌሎችም የልቅናና የምሉዕነት መገለጫዎችን ለአሏህ እያረጋገጠ ነው።
ሱነን ቲርሚዚ (5/ 385) (3370).
ሱነን ኢብኑ ማጀህ (5/ 6) (3829).
ሙስነድ አሕመድ (14/ 360) (8748).
ተጨማሪ (8)
توضيح الأحكام من بلوغ المرام.
للبسام (7/ 546).
منحة العلام في شرح بلوغ المرام.
لعبد الله الفوزان (10/ 416).
فتح ذي الجلال والإكرام.
لابن عثيمين (6/ 481).
سبل السلام بشرح بلوغ المرام.
للصنعاني (2/ 707).