Skip to content

'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡

'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"

«أَكْمَلُ الْمُؤْمِنِينَ إِيمَانًا أَحْسَنُهُمْ خُلُقًا، وَخَيْرُكُمْ خَيْرُكُمْ لِنِسَائِهِمْ».

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ሐሰን ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች መካከል ኢማኑ የሞላው ስነምግባሩ ያማረ ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለሰዎች ፊቱን ፈታ በማድረግ፣ መልካምን በመስጠት፣ ንግግርን በማሳመርና ሰዎችን ከማወክ በመቆጠብ ነው። ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ለምሳሌ ለሚስቱ፣ ለሴት ልጆቹ፣ ለእህቶቹና ለቅርብ ዘመዶቹ ምርጥ የሆኑ ናቸው። ምክንያቱም ሴቶች በመልካም ስነምግባር ሊኗኗራቸው ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የተገቡ ስለሆኑ ነው።

የቃላት ፍቺ

....:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የመልካም ስነምግባር ትሩፋትን እንረዳለን። እሱ ከኢማን የሚመደብ ነውና።

ተግባር ከኢማን የሚመደብ መሆኑን፤ ኢማን ይጨምራልም ይቀንሳልም።

ኢስላም ሴቶችን የሚያከብር እምነት መሆኑንና ለሴቶች መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱንም እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (7/ 70) (4682).

ሱነን ቲርሚዚ (2/ 454) (1162).

ተጨማሪ (9)

مسند أحمد ط الرسالة (12/ 364) (7402).

سلسلة الأحاديث الصحيحة وشيء من فقهها وفوائدها.

للألباني (1/ 573).

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 362).

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (3/ 130).

كنوز رياض الصالحين.

لمجموعة من الباحثين (5/ 234).