"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር።
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር። በረመዷን ውስጥም በየሁሉም ምሽት ያገኛቸውና ቁርአን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ንፋስም የበለጠ በመልካም ነገር ላይ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ።"
كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ، وَكَانَ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ فَيُدَارِسُهُ القُرْآنَ، فَلَرَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدُ بِالخَيْرِ مِنَ الرِّيحِ المُرْسَلَةِ.
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው: የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው። ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቸርነት፣ የደግነታቸው ስፋት መገለፁ። በተለይ በረመዷን ወር። ይህም ወሩ የአምልኮ ወርና የመልካም መሸመቻ ወር ስለሆነ ነው።
በሁሉም ወቅት ቸር በመሆን ላይ መነሳሳቱንና በረመዷን ወር ደግሞ ቸርነትን መጨመር እንደሚገባ እንረዳለን።
በረመዷን ወር አብዝቶ መለገስ፣ መስጠት፣ በጎ መስራትና ቁርአን መቅራት እንደሚገባ እንረዳለን።
እውቀትን ለመሸምደድ ከሚረዱ ሰበቦች አንዱ ከእውቀት ፈላጊዎችና ዑለሞች ጋር መማማሩ ነው።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 8) (6).
ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 1803) (2308).
ተጨማሪ (8)
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (5/ 275).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
مجموعة من الباحثين (2/ 870).
بهجة الناظرين.
لسليم الهلالي (2/ 364).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين.
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
9 መጻሕፍት- የረመዳን ወርን የተመለከቱ ጥያቄዎችና መልሶች ለህፃናት እና ለአዋቂዎች"የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ለጋስ ነበሩ፤ የበለጠ ለጋስና ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ጂብሪልም በሚያገኛቸው ጊዜ ነበር። ጂብሪል በረመዳን በየሌሊቱ ያገኛቸውና ቁርኣንን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ነፋስ የበለጠ በመልካም ነገር ላይ ፈጣን ነበሩ።"
- የረመዳን ወርን የተመለከቱ ጥያቄዎችና መልሶች ለህፃናት እና ለአዋቂዎች"(የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና)) የበለጠ ለጋስና ቸር የሚሆኑት በረመዳን ጂብሪል በሚያገኛቸው ጊዜ ነበር። ጂብሪል በረመዳን በየሌሊቱ ያገኛቸውና ቁርኣንን ያስተምራቸው ነበር።"
ተጨማሪ (7)
- تطبيق القرآن والأذكارسنن الصيام (كان رسول الله - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - أجود الناس بالخير، وكان أجود ما يكون في رمضان حين يلقاه جبريل، وكان جبريل يلقاه في كل ليلة من رمضان، فيدارسه القرآن، فلرسول الله - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - حين يلقاه جبريل أجود
- سنن الصيام - من كتاب الفقه الميسرسنن الصيام(كان رسول الله - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - أجود الناس بالخير، وكان أجود ما يكون في رمضان حين يلقاه جبريل، وكان جبريل يلقاه في كل ليلة من رمضان، فيدارسه القرآن، فلرسول الله - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - حين يلقاه جبريل أجود
- مشروع منهاج زادكزادك 2 طالب نهائي«كَانَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ»
- مشروع منهاج زادكزادك 2 طالب نهائي«كَانَ جِبْرِيلُ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ فَيُدَارِسُهُ القُرْآنَ»
- نبراس طالب (3)نبراس طالب 3«كَانَ جِبْرِيلُ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ فَيُدَارِسُهُ القُرْآنَ»
- نبراس طالب (3)نبراس طالب 3«كَانَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ»
- نصوص مختارة للرمضانكَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ