Skip to content

"በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።"

ከመዕቂል ቢን የሳር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:

"በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።"

«الْعِبَادَةُ فِي الْهَرْجِ كَهِجْرَةٍ إِلَيَّ».

ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በፈተና፣ በጦርነት፣ የሰዎች ጉዳይ ውጥንቅጡ በወጣ ወቅት አምልኮ ላይ መትጋትን ጠቆሙ። በዚህ ወቅት አምልኮ የማድረግ ምንዳም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስደት እንደማድረግ መሆኑንም ተናገሩ። ይህም የሆነበት ሰዎች ከአምልኮ የሚዘናጉበትና ጥቂቶች ካልሆኑ በቀር አምልኮ ላይ የማይሳተፉበት ወቅት ስለሆነ ነው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በፈተና ቀናት ከፈተናው ለመጠበቅና ከብክለት ለመዳን አምልኮ በማድረግና ወደ አላህ በመዞር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

በፈተናና በዝንጉነት ወቅት የአምልኮ ትሩፋት መገለፁ።

አንድ ሙስሊም የፈተናና የዝንጉነት ስፍራዎችን መራቅ እንደሚገባው ያስረዳናል።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2268) (2948).

ተጨማሪ (4)

كشف المشكل من حديث الصحيحين (2/ 42).

البحر المحيط الثجاج في شرح صحيح الإمام مسلم بن الحجاج (45/ 5).

بهجة الناظرين (2/ 455).

نزهة المتقين (ص942).