"አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦
"አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?" እኛም "አዎን" አልን። እሳቸውም "አንዳችሁ በሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸው ሶስት አንቀፆች ከሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎች ለሱ የተሻሉ ናቸው።" አሉ።
«أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ إِذَا رَجَعَ إِلَى أَهْلِهِ أَنْ يَجِدَ فِيهِ ثَلَاثَ خَلِفَاتٍ عِظَامٍ سِمَانٍ؟» قُلْنَا: نَعَمْ. قَالَ: «فَثَلَاثُ آيَاتٍ يَقْرَأُ بِهِنَّ أَحَدُكُمْ فِي صَلَاتِهِ خَيْرٌ لَهُ مِنْ ثَلَاثِ خَلِفَاتٍ عِظَامٍ سِمَانٍ».
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰላት ውስጥ ሶስት አንቀፆችን በማንበብ የሚገኘው ምንዳ አንድ ሰው ቤቱ ውስጥ ሶስት የሰቡ ትላልቅ እርጉዝ ግመሎችን ከሚያገኝ እንደሚበልጥ ገለፁ።
...:
ሰላት ውስጥ ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት መገለፁ።
መልካም ሥራዎች ከጠፊዋ ዱንያ መጣቀሚያ የተሻሉና ዘውታሪዎች ናቸው።
ይህ ትሩፋት ሦስት አንቀፆችን በማንበብ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰጋጁ ሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸውን አንቀፆች በጨመረ ቁጥር የሚያገኘው ምንዳ ለሱ በሚያነባቸው ቁጥር ልክ የእርጉዝ ግመሎች ከሚሰጠው የተሻለ ነው።
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 552) (802).
ተጨማሪ (4)
إكمال المعلم (3/172).
الإفصاح عن معاني الصِّحاح (8/65).
فتح المنعم شرح صحيح مسلم (3/620).
البحر المحيط الثجاج (16/343).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
2 መጻሕፍትተጨማሪ (2)
- الذكر والدعاء والعلاج بالرقي من الكتاب والسنة"أيحب أحدكم إذا رجع إلى أهله أن يجد فيه ثلاث خَلِفَاتٍ عِظامٍ سمانٍ؟ " قلنا نعم.
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“أيحب أحدكم إذا رجع إلى أهله أن يجد فيه ثلاث خلفات عظام سمان؟” قلنا: نعم، قال: “فثلاث آيات يقرأ بهن أحدكم في صلاته، خير له من ثلاث خلفات عظام سمان”.