Skip to content

"አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!"

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

"አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!"

«يَسِّرُوا وَلَا تُعَسِّرُوا، وَبَشِّرُوا وَلَا تُنَفِّرُوا».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ዓለማዊም ይሁን ዲናዊ በሆኑ ጉዳዮች ለሰዎች ማቅለልና ማግራራትን እንዲሁም እነርሱ ላይ አለማክበድን አዘዙ። ይህም ማግራራት አላህ በፈቀደውና በደነገገው ድንበር ውስጥ ሆኖ ነው። ሰዎችን በመልካም ነገሮች በማበሰርና እነርሱን ከመልካም ነገሮች ባለማሸሽ ላይም አበረታቱ።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የአንድ አማኝ ግዴታ ሰዎች አላህን እንዲወዱ ማድረግና በመልካም ነገሮች ላይ ማነሳሳት ነው።

ወደ አላህ የሚጣራ ሰው የኢስላምን ጥሪ ወደ ሰዎች በጥበብ እንዴት እንደሚያደርስ ማስተዋል ይገባዋል።

ማበሰር ለዳዒውም ለሚያስተላልፈው ነገርም ደስታን ተሰሚነትንና መረጋጋትን ያስተርፋል።

ማካበድ በዳዒው ንግግር ውስጥ ማሸሽን ፣ ተቀባይነት ማጣትና ጥርጣሬን ይፈጥራል።

ለነርሱ የወደደላቸው ገር እምነትና ቀላል ድንጋጌ በመሆኑ አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን እንረዳለን።

እንድናግራራ የታዘዝንባቸውን ነገሮች ማግራራት ሸሪዓ ይዞት የመጣው አንዱ ድንጋጌ ነው።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 25) (69).

ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1358) (1732).

ተጨማሪ (6)

شرح صحيح البخاري.

لابن بطال (1/ 153).

إرشاد الساري لشرح صحيح البخاري.

لأبو العباس القسطلاني (1/ 169).

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 687).