ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ
ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሀኒይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሑደይቢያ ምሽት የዘነበን ዝናብ አስከትለው የንጋትን (የሱብሒን) ሰላት አሰገዱን። ሰላቱን ያጠናቀቁ ጊዜም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ "ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ። በአላህ ችሮታና እዝነት ምክንያት ዘነበልን ያለ በኔ ያመነ በከዋክብት የካደ ነው። በእንዲህ እንዲህ የኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን ያለ ደግሞ በኔ የካደና በከዋክብት ያመነ ነው።"
صَلَّى لَنَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ صَلَاةَ الصُّبْحِ بِالْحُدَيْبِيَةِ عَلَى إِثْرِ سَمَاءٍ كَانَتْ مِنَ اللَّيْلَةِ، فَلَمَّا انْصَرَفَ أَقْبَلَ عَلَى النَّاسِ، فَقَالَ: «هَلْ تَدْرُونَ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ؟» قَالُوا: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «أَصْبَحَ مِنْ عِبَادِي مُؤْمِنٌ بِي وَكَافِرٌ، فَأَمَّا مَنْ قَالَ: مُطِرْنَا بِفَضْلِ اللهِ وَرَحْمَتِهِ، فَذَلِكَ مُؤْمِنٌ بِي وَكَافِرٌ بِالْكَوْكَبِ، وَأَمَّا مَنْ قَالَ: بِنَوْءِ كَذَا وَكَذَا، فَذَلِكَ كَافِرٌ بِي وَمُؤْمِنٌ بِالْكَوْكَبِ».
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሑደይቢያ (መካ አቅራቢያ የምትገኝ መንደር ናት) የንጋት (የሱቢሕ) ሰላትን በዛ ምሽት ዝናብ ከዘነበ በኋላ አሰገዱ። ሰላቱን በማሰላመት ያጠናቀቁ ጊዜ ፊታቸውን ወደ ሰዎች በመዞር "የተከበረውና የላቀው ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" በማለት ጠየቋቸው። ሰሓቦችም አላህና መልክተኛው ያውቃሉ በማለት መለሱላቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ " ከፍ ያለው አላህ ሰዎች ዝናብ በሚዘንብ ወቅት ለሁለት እንደሚከፈሉ ገለፀ። አንዱ ክፍል በአላህ አማኝ የሆነ ክፍል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአላህ ከሀዲ የሆነ ክፍል ነው።" በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን በማለት የዝናብን መውረድ ወደ አላህ ያስጠጋ ሰው ይህ ፈጣሪና የዩንቨርሱ አስተናባሪ በሆነው አላህ ያመነ በከዋክብት ደግሞ የካደ መሆኑን፤ በእንዲህ እንዲህ ኮኮብ ዘነበልን ያለ ደግሞ በአላህ የካደና በከዋክብት ያመነ መሆኑን ገለፀ። ይህ ክህደት የዝናብን መውረድ ወደ ከዋክብት ከማስጠጋቱ አንፃር ትንሹ ኩፍር ነው። ምክንያቱም አላህ በሸሪዐም ሆነ በውሳኔ ዝናብ ለመዝነብ ሰበብ አላደረገውምና ነው። የዝናብን መውረድና ሌሎች ምድራዊ ክስተቶችን ከዋክብት ለመውጣትና ለማረፍ (ለመውደቅ) ወደሚያደርጉት እንቅስቃሴ ያስጠጋና ከዋክብት ትክክለኛ አስተናባሪ መሆናቸውን ያመነ ትልቁን ክህደት የካደ ይሆናል።
...:
ከዝናብ መውረድ በኋላ፦ በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
የዝናብ መውረድና ሌሎችን ፀጋዎች መፍጠሩንና ማስገኘቱን ወደ ከዋክብት ያስጠጋ ትልቁን ክህደት የካደ ሲሆን ወደ ከዋክብት በሰበብ ደረጃ ካስጠጋ ደግሞ ትንሹን ክህደት የካደ ይሆናል። ምክንያቱም ሸሪዐዊም ሆነ ህዋሳዊ ሰበብ አይደለምና።
አንድ ፀጋ በተካደ ጊዜ የክህደት ምክንያት ሲሆን፤ ተገቢ ምስጋና ከቀረበበት ደግሞ የኢማን ምክንያት ይሆናል።
የሽርክን መዳረሻ ለመዝጋት ሲባል ወቅቱን ለመግለፅ ተፈልጎበት ቢሆን እንኳን "በእንዲህ ኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን" ማለት መከልከሉን እንረዳለን።
ፀጋን በማምጣትና መአትን በመከላከል ረገድ ቀልብን በአላህ ላይ ማንጠልጠል ግዴታ መሆኑን ተረድተናል።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 169) (846).
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 83) (71).
ተጨማሪ (2)
البحر المحيط الثجاج في شرح صحيح الإمام مسلم بن الحجاج (2/ 484).
المفهم لما أشكل من تلخيص كتاب مسلم (1/ 260).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
3 መጻሕፍትተጨማሪ (3)
- التوحيد في ضوء عقيدة الإمام الشافعي رحمه الله ونصوصه ومروياته"صلى لنا رسول الله صلى الله عليه وسلم صلاة الصبح بالحديبية على إثر سماء كانت من الليل، فلما انصرف أقبل على الناس فقال: هل تدرون ماذا قال ربكم؟. قالوا: الله ورسوله أعلم، قال: قال: أصبح من عبادي مؤمن بي وكافر، فأما من قال: مطرنا بفضل الله ورح
- محرمات استهان بها كثير من الناسصلى لنا رسول الله صلى الله عليه وسلم صلاة الصبح بالحديبية على أثر سماء كانت من الليلة، فلما انصرف أقبل على الناس، فقال: هل تدرون ماذا قال ربكم؟ قالوا: الله ورسوله أعلم، قال: " أصبح من عبادي مؤمن بي وكافر، فأما من قال مطرنا بفضل الله ورحمته
- موسوعة الإيمان«أَصْبَحَ مِنْ عِبَادِي مُؤْمِنٌ بِي وَكَافِرٌ، فَأَمَّا مَنْ قَالَ: مُطِرْنَا بِفَضْلِ اللَّهِ وَرَحْمَتِهِ، فَذَلِكَ مُؤْمِنٌ بِي وَكَافِرٌ بِالكَوْكَبِ، وَأَمَّا مَنْ قَالَ: بِنَوْءِ كَذَا وَكَذَا، فَذَلِكَ كَافِرٌ بِي وَمُؤْمِنٌ بِالكَو