'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች)
ከዐብደሏህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች) ጠፉ!' ሶስት ጊዜ ደጋገሟት።"
«هلك المُتَنَطِّعُون» قالها ثلاثًا.
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ያመጡትን ሸሪዓዊ ወሰን ያለ ምንም መመሪያና እውቀት ወሰን ተላልፈው በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው በእምነታቸውም ይሁን በአለማዊ ጉዳያቸው ፅንፍ የሚረግጡ ሰዎች ያለባቸውን ውርደትና ኪሳራ ተናገሩ።
....:
በየትኛውም ጉዳይ በተለይም በዒባዳና ፃድቃንን በማላቅ ረገድ ወሰን ማለፍና ያላቅም መንጠራራት መከልከሉንና ከእንዲህ አይነቱ ነገር መራቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ እንደሚበረታታ እንረዳለን።
በአምልኮም ይሁን በሌላው ጉዳይ ተስተካክሎ የተሟላውን መፈለግ እንደሚገባና ይህም የሚሆነው ሸሪዓውን በመከተል መሆኑን እንረዳለን።
አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ጠንከር ማድረግ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንኑ እንኳ ሲናገሩ ሶስት ጊዜ ደጋግመው ነውና የተናገሩት።
የእስልምና ገራገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።
ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2055) (2670).
ተጨማሪ (4)
الجديد في شرح كتاب التوحيد.
للقرعاوي (ص180).
الملخص في شرح كتاب التوحيد.
لصالح الفوزان (ص167).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
4 መጻሕፍትተጨማሪ (4)
- حراسة التوحيدإقامة البراهين على حكم من استغاث بغير الله«هَلَكَ المُتَنَطِّعُونَ» قَالَهَا ثَلَاثًا.
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «هَلَكَ الْمُتَنَطِّعُونَ» قَالَهَا ثَلاَثاً.
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 8«هَلَكَ المُتَنَطِّعُونَ» قَالَهَا ثَلاثاً.
- مجموعة زاد الحديث(2)1«هلك المتنطعون - قالها ثلاثا»