Skip to content

"ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

"ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"

«كَلِمَتَانِ خَفِيفَتَانِ عَلَى اللِّسَانِ، ثَقِيلَتَانِ فِي الْمِيزَانِ، حَبِيبَتَانِ إِلَى الرَّحْمَنِ: سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيمِ، سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ ያለምንም መጨናነቅና በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ ስለሚናገራቸው ሁለት ቃላቶች ነገሩን። እነሱም ምንዳቸው ሚዛን ላይ የገዘፈ፣ ጌታችን አር‐ራሕማንም የሚወዳቸው ናቸው። "ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ" የሚሉት ናቸው። ደረጃቸው የላቀበትም ምክንያት የአላህን የልቅናና የምሉዕነት ባህሪያት የያዙ ፤ የላቀውንና የጠራውን አላህንም ከጉድለቶች ስለሚያጠሩ ነው።

የቃላት ፍቺ

.....:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በላጩ ውዳሴ አላህን ማጥራትና ማወደስን የሰበሰበ ውዳሴ ነው።

አላህ በጥቂት ስራ ብዙ ምንዳ መመንዳቱ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን ይገልፅልናል።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 86) (6406).

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2072) (2694).

ተጨማሪ (4)

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (10/ 480).

فتح ذي الجلال والإكرام بشرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (6/ 519).