Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 81 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (52)
"ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሱብሓነሏሂል ዐዚም ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ጀነት ውስጥ ለርሱ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የአላህንም ቤት ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉና ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "የመልካም ነገሮችን በር አልጠቁምህምን? ጾም ጋሻ ነው፤ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ምፅዋትም ወንጀልን ታጠፋለች፤ የሰውዬው በሌሊቱ አጋማሽ የሚሰግደው ሶላት" አሉና ቀጥለው {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} ከሚለው {ይሰሩትም በነበሩት} እስከሚለው ድረስ [ሱረቱ ሰጅዳ: 16‐17] አነበቡ። ቀጥለውም "የነገሩ ሁሉ ራስ፣ ምሰሶውንና ሻኛውን ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። እርሳቸውም "የነገሮች ሁሉ ራስ (ዋና) እስልምና ነው፤ ምሰሶው ሶላት ነው፤ ሻኛው ጂሃድ ነው።" አሉ። ቀጥለውም "ይህን ሁሉ የሚቆጣጠረውን ነገር ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ ነቢይ ሆይ!" አልኳቸው። ምላሳቸውን ያዙና "በራስህ ላይ ይህቺን ቆጥባት!" አሉ። እኔም "የአላህ ነቢይ ሆይ! እኛ በምንናገረው እንያዛለንን?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ትጣህና ሙዓዝ ሆይ! ምላሳቸው ያጨደችው ካልሆነ በቀር ሰዎችን በፊታቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ነጭ ልብስ ምርጡ ልብሳችሁ ነውና ከልብሶቻችሁ መካከል ነጩን ልብስን ልበሱ። ሟቾቻችሁንም በርሱ ከፍኑ።"»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።