Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 64 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም ወደ ቀኝ ይመለከታል። ያሳለፈውን እንጂ ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራም ይመለከታል ካሳለፈው በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ይመለከታል በፊትለፊቱ ከእሳት ውጭ ሌላ ምንም አይመለከትም። በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግመል ላይ ሆነው ሙዓዝ ከኋላ ተፈናጦ ሳለ እንዲህ አሉ: 'አንተ ሙዓዝ ቢን ጀበል ሆይ' እርሱም ሶስቴ 'ለጥሪዎት ደጋግሜ አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አሁንም 'ሙዓዝ ሆይ!' አሉት: እሱም 'ለጥሪዎት ደጋግሜ አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አለ። ሶስት ጊዜ ደገሙትና ቀጥለውም ' አንድም በእውነተኛ ልቡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር የለም አላህ በእርሱ ላይ እሳትን እርም ቢያደርግ እንጂ።' አሉ። እርሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህንን ለሰዎች ነገሬ ላበስራቸው እንዴ?' አለ። እሳቸውም 'ከነገርካቸውማ (በዚህ ሐዲሥ ላይ) ይደገፋሉ (ይሰንፋሉ)።' አሉ። ሙዓዝ ይህንን ሐዲስ የተናገረው ወንጀል ውስጥ ላለ መውደቅ ብሎ ሊሞት ሲል ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰዎች የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለጠንቋዮች ጠየቁ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነርሱ 'ምንም አይደሉም።' በማለት መለሱ። እነሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ተናግረው እውነት ይሆናል።' አሉ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ' ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል። እርሱን መገዛታችሁን፣ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታችሁን፣ ሁላችሁም በአላህ ገመድ መተሳሰራችሁንና አለመለያየታችሁን ለናንተ ይወድላችኋል። አሉባልታን፣ ጥያቄ ማብዛትንና ገንዘብ ማባከንን በናንተ ላይ ይጠላባችኋል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአሸጅ ዐብዲል ቀይስ እንዲህ አሉ: "አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።