Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።
"አንድ ሰውዬ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣና በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አውርቷቸው 'የአላህና የእርሶ መሻት ሆነ።' አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ለአላህ ቢጤ አደረግከኝን? የብቸኛው አላህ መሻት ሆነ! በል!' አሉት።"
ሰነዱ ሐሰን ነው። رواه ابن ماجه والنسائي في الكبرى وأحمد
"አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።"»
ነወዊይ ሐዲሡ ሐሰን ነው ብለዋል ኢብኑ ማጃህ እና አል-በይሀቂይ እንዲሁም ሌሎችም ዘግበውታል
"ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተወሰኑ ሰዎች መጡ። ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋቡና ከአንዱ ጋር ቃልኪዳን ከመጋባት ተቆጠቡ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋብተው ይህንን ለምን ተዉ?' አሉ። እርሳቸውም 'እርሱ ላይ ሒርዝ ስላለ ነው።' አሉ። (ይህንን ሲሰማ) እጁን አስገባና ቆረጠው። እርሳቸውም ቃልኪዳን ተጋቡትና 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።"
ሐሰን ነው። አሕመድ ዘግበውታል።