Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 8 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት። ከላይ ያለች እጅ ሰጪዋ ስትሆን ከታች ደግሞ ጠያቂዋ እጅ ናት።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም ወደ ቀኝ ይመለከታል። ያሳለፈውን እንጂ ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራም ይመለከታል ካሳለፈው በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ይመለከታል በፊትለፊቱ ከእሳት ውጭ ሌላ ምንም አይመለከትም። በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በአላህ መንገድ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ባሪያ ነፃ ለማውጣት ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለሚስኪን ምፅዋት ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለቤተሰቦችህ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር መካከል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ለቤተሰብህ ወጪ ያደረግከው ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት ልትለምነኝ መጣች። እኔ ዘንድም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስሰጣት ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገርኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መካከል የተወሰኑት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሀብት ባለቤቶች በምንዳ ጥለውን ሄዱ። እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመው ይጾማሉ፤ በትርፍ ገንዘቦቻቸው ይመፀውታሉ።" እርሳቸውም "አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላበረደ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "እስኪ ንገሩኝ ብልቱን ሐራም ላይ ቢያኖራት ኖሮ ወንጀል አይኖርበትም ነበርን? ልክ እንደዚሁ የተፈቀደችለት ባለቤቱ ላይ ያኖራት ጊዜም ለርሱ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።