Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 11 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
"መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።"»
በሌላ ምክንያት ሐሰን የሆነ (ሐሰን ሊገይሪሂ) ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
«እነርሱ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ እየበላን አንጠግብም።" አሏቸው። እርሳቸውም "ምናልባት ተበታትናችሁ ለየብቻ እየበላችሁ ይሆን?" ብለው ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን" አሉ። እርሳቸውም "ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።"»
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"የሥራ ዓይነቶች ስድስት ሲሆኑ፤ የሰው ዓይነቶች ደግሞ አራት ናቸው። (የሥራ ዓይነቶች) ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉ፣ አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ፣ በአስር ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ፣ በሰባት መቶ ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ ናቸው። ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉት፥ በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ደግሞ እሳት ገባ። አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ ደግሞ፥ ቀልቡ እንደሚሠራው እስኪሰማውና አላህ የሱን (ቁርጠኝነት) እስኪያውቅለት ድረስ መልካም ስራ ለመሥራት ያሰበ (ከዛም ካልሰራው) አንድ መልካም ሥራ ተብሎ ይጻፍለታል፤ መጥፎ ሥራን የሠራ አንድ መጥፎ ሥራ ተብሎ ይፃፍበታል። አንድ መልካም ሥራን የሠራ ምንዳው በአስር ተባዝቶ ይፃፍለታል። በአላህ መንገድ ላይ አንዲትን ምፅዋት የመፀወተ ምንዳው እስከ ሰባት መቶ ተባዝቶ ይጻፍለታል። የሰዎች ዓይነት ደግሞ ዱንያ ለሱ የሰፋችለት አኺራው ግን የተጣበበበት፣ዱንያ ለሱ የጠበበችበት አኺራ ግን የሰፋችለት፣ ዱንያም አኺራም ለሱ የተጣበቡበት፣ ዱንያም አኺራም ለሱ የሰፉለት ናቸው።
ሐሰን ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
"አማና (አደራ) የሌለው ሰው ኢማን የለውም፤ ቃልኪዳን የማያከብር የሆነ ሰው ሃይማኖት የለውም።"»
በሌላ ምክንያት ሐሰን የሆነ (ሐሰን ሊገይሪሂ) አሕመድ ዘግበውታል።
«አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሀያ" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሰላሳ" አሉ።»
ሐሰን ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ አሕመድ እና ዳሪሚይ ዘግበውታል
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።
ሐሰን ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
«"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።»
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።