Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 7 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝ። በኔ ላይም ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በወፍጮ ምክንያት እጇ ላይ ስለሚያጋጥማት ጉዳይ ለማማከር መጣች። እርሳቸው ዘንድ ባሪያ እንደመጣም ወሬ ደረሳት። ቤት ስትሄድም አላገኘቻቸውምና ይህንን ለዓኢሻ አወሳችላት። እርሳቸው ሲመጡም ዓኢሻ ለርሳቸው ነገረቻቸው። ዓሊይ እንዲህ አለ: «መኝታችን ላይ ሆነን ሳለ መጡ። ለመነሳት ስንዘጋጅም "ባላችሁበት ሁኑ" አሉንና መጥተው የእግራቸው ቅዝቃዜን ሆዴ እስኪሰማው ድረስ በኔና በርሷ መካከል መጥተው ተቀመጡና እንዲህ አሉ: "ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ንፋስን አትሳደቡ! የምትጠሉትን ነገር በተመለከታችሁ ጊዜ "አላህ ሆይ! ከዚህች ንፋስ መልካሙን፣ በውስጧ የያዘችውንም መልካም ነገር፣ የታዘዘችውንም መልካም ነገር እንጠይቅሃለን፤ ከዚህች ንፋስ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጎጂ ነገር፣ ከታዘዘችውም መጥፎ ነገር በአንተ እንጠበቃለን።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ በ "አልኩብራ" ውስጥ እና አሕመድ ዘግበውታል
"በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።