Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 27 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መካከል የተወሰኑት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሀብት ባለቤቶች በምንዳ ጥለውን ሄዱ። እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመው ይጾማሉ፤ በትርፍ ገንዘቦቻቸው ይመፀውታሉ።" እርሳቸውም "አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላበረደ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "እስኪ ንገሩኝ ብልቱን ሐራም ላይ ቢያኖራት ኖሮ ወንጀል አይኖርበትም ነበርን? ልክ እንደዚሁ የተፈቀደችለት ባለቤቱ ላይ ያኖራት ጊዜም ለርሱ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራን በርሱ ጀልባዎቻችን ይለቀለቃሉ፣ ቆዳችንን እንቀባበታለን፣ ሰዎች በርሱ መብራትን በመስራት ይጠቀማሉ። ንገሩን እርሱም ክልክል ነውን?" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱም ክልክል ነው።" አሉና ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉ "አላህ የሁዶችን ረገመ። አላህ ሞራን ከመጠቀም የከለከላቸው ጊዜ አሳምረው ሸጡትና የሸጡበትን ዋጋ በሉት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የተከለከለው ክልል ውስጥ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል