Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 27 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው) ታማኝ የምንሆነው?" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለውም በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፤ ምጽዋት ማስረጃ ነው፤ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፤ ቁርኣን ወይ ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰዎች በሙግታቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይሞግቱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
ሐሰን ነው። በይሀቂይ እና ሌሎችም በዚህ መልኩ ዘግበውታል፤ ከፊሉም በሁለቱ ሶሒሖች ውስጥ ይገኛል።
"በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ብሎ የሆነ ሰው (ምንዳውም) ለአላህና ለመልእክተኛው ሆኖለታል፤ የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ወይም ሴትን ለማግባት ብሎ የተሰደደ ሰውም የስደቱ (ምንዳ) ለተሰደደለት ጉዳይ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ሁለቱ የሐዲሥ ሊቃውንት ኢማሞች (መሪዎች) አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ቢን ኢስማዒል ቢን ኢብራሂም ቢን አል-ሙጊራህ ቢን በርዲዝበህ አል-ቡኻሪ እና አቡል ሑሰይን ሙስሊም ቢን አል-ሐጃጅ ቢን ሙስሊም አል-ቁሸይሪይ አን-ነይሳቡሪይ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ይበልጥ ትክክለኛ በሆኑት በሁለቱ ሰሒሕ መጻሕፍቶቻቸው ውስጥ ዘግበውታል።