Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 16 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ከጃቢር ሐዲሥ ዘግበውታል፤ ሙስሊምም ከሑዘይፋ ሐዲሥ ዘግበውታል
"ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም 'ሶላትን በወቅቱ መስገድ።' አሉ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ቀጥሎ ለወላጆች መልካም መዋል ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። እነዚህን ነገሩኝ። ጥያቄዬን ብጨምር እርሳቸውም ይጨምሩልኝ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።
"ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።