Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 17 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"
ሐሰን ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ "አልኩብራ" ውስጥ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
"አዋጅ! ዱንያ የተረገመች ናት። አላህን ማውሳት፣ አላህን ከማውሳት ጋር የተቆራኘ፣ ዐዋቂ (ዐሊም) ወይም ዕውቀት ፈላጊ ካልሆነ በቀር በዱንያ ውስጥ ያለውም የተረገመ ነው።"
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።"
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
"ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ቀብር የመጪው ዓለም የመጀመሪያው ማረፊያ ነው። ከቀብር (ቅጣት) ከዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ከርሱ የበለጠ ቀላል ነው። ከቀብር (ቅጣት) ካልዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
‹እንዲህ በል: አልላሁመክፊኒ ቢሐላሊከ ዐን ሐራሚክ፤ ወአግኒኒ ቢፈድሊከ ዓመን ሲዋክ›"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በሐላልህ ከሐራምህ ጠብቀኝ፤ በችሮታህም ከአንተ ውጪ ካሉ አብቃቃኝ።" ማለት ነው።
ሐሰን ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} [አትተካሡር: 8] የሚለው አንቀፅ የወረደ ጊዜ ዙበይር እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንመገብ የነበረው ሁለቱን ጥቁሮች ተምርና ውሃ ነው። ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው?" እሳቸውም "እርሱኑ ሳይሆን አይቀርም የምትጠየቁት።" አሉት።
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
"ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።»
ነወዊይ ሐዲሡ ሐሰን ነው ብለዋል ኢብን ማጃህ እንዲሁም ሌሎችም ጥሩ በሆኑ ሰነዶች ዘግበውታል