Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 66 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«በአንድ ምሽት የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከፍራሼ ላይ አጣኋቸው። በዳሰሳ ስፈልጋቸውም እጄ መስገጃቸው ላይ የተተከለችው የእግራቸው ውስጥ ላይ አረፈች። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር " አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር ‹ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ› ትርጉሙም 'ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«"ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አረንጓዴ አታክልት ያለበት ድስት መጣላቸው። ውስጡም የሆነ ጠረን ሸተታቸው። ሲጠይቁም ውስጡ ስላለው ቡቃያ ተነገራቸው። እርሳቸውም ከርሳቸው ጋር ወደነበረ አንድ ባልደረባቸው "አስጠጉት" አሉ። እሳቸው መብላቱን እንደጠሉ ሰውየው መመልከቱን ባስተዋሉ ጊዜ እርሳቸውም "ብላ እኔ አንተ የማታወራው ጋር ስለማወራ ነው።" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።