Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 66 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
የተወሰኑ ሰዎች የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሚንበር ከምን አይነት እንጨት ነው የተሰራው? በሚለው ተከራክረው ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ዘንድ መጡ። ስለጉዳዩም ጠየቁት። እርሱም "ወላሂ እኔ ከምን እንደተሰራ አውቃለሁ። መጀመሪያ የተኖረበት ቀንና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሱ ላይ መጀመሪያ የተቀመጡ እለት ተመልክቼዋለሁ። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ እከሊት (ከአንሷር የሆነች ሴት ስትሆን ሰህል ስሟን ጠርቷት ነበር።) "አናጢውን አገልጋይሽን ለሰዎች ንግግር ሳደርግ የምቀመጥበትን እንጨት እንዲሰራልኝ እዘዢ።" በማለት መልእክት ላኩላት። እርሷም አዘዘችው። እርሱም ሚንበሩን ‹ጦርፋኡል ጛባ› (ጠደቻ) ከሚባለው የእንጨት አይነት ሰርቶ ወደርሷ አመጣ። እርሷም ወደ አላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላከችው። በርሳቸው ትእዛዝም እዚህ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሱ ላይ ሲሰግዱበት ተመልክቻቸዋለሁ። ሚንበሩ ላይ እንዳሉ ተክቢራ አደረጉ ፣ እዛው ላይ እያሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ወደኋላ ወረዱ፣ ከሚንበሩ ስር ሱጁድ አደረጉና እንደገና ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። ሶላቱን ያጠናቀቁ ጊዜ ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ 'እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ። በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ።" ቀጥለው በሶስተኛው "ለፈለገ ሰው" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።" ቀጥሎም አቡ ሁረይራ እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {የጎህ ሶላት ( መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78]»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ኢብኑ ዙበይር በሁሉም ሶላት ካሰላመተ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር። 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁ አንኒዕመህ ወለሁልፈድል ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን፤ ላኢላሃ ኢለሏሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሃል ካፊሩን' አስከትለውም እንዲህ አሉ ' የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' (ኑ ወደ ሶላት) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' (ኑ ወደ ስኬት!) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሃትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜም 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ያለ ጊዜም 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' ካለ ጀነት ገባ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል